የስንብት እርምጃና የጊዜ ገደብ


የሰ/መ/ቁ. 36377

ኀዳር 2 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.

ዳኞች፡- አብዱልቃድር መሐመድ

ሐጎስ ወልዱ

ሒሩት መለሠ

ተሻገር ገ/ሥላሴ

ሱልጣን አባተማም

አመልካች፡- የኢትዮጵያና የጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት – ወይንሸት እንድሪስ ቀረበ፡፡

ተጠሪ፡- ተሾመ ኩማ ቀረበ፡፡

መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍ ር ድ

በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁ. 377/96 መሠረት የሚታይ የስራ ክርክር የሚመለከት ነው፡፡ ከመዝገቡ እንደሚታየው ክርክሩ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ነው፡፡ በአመልካች ላይ ከሰ የመሠረተውም የስራ ውሌ ከሕግ ውጪ ተቋርጦብኛል፡፡ ስለዚህም ውዝፍ ደመወዜ ተከፍሎኝ ወደ ስራዬ እንድመለስ ይወሰንልኝ በማለት ነው፡፡ አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ የሥራ ውሉ የተቋረጠው ተጠሪ በፈጸመው ሕገወጥ ድርጊት ምክንያት ነው፡፡ ድርጊቱ ከሥራ የሚያሰናብት ነው በማለት የተከራከረ ሲሆን ፍ/ቤቱም ክርክሩን ከሰማ በኋላ፣ አመልካች የሥራ ውል የማቋረጥ እርምጃ የወሰደው ድርጊቱ ከተፈጸመ ከአንድ ወር በኋላ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት ተጠሪ የስድስት ወር ደመወዝ ተከፍሎት ወደ ሥራው እንዲመለስ ወስኖአል፡፡ በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠው ብይን ጉድለት የለበትም ብሎአል፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው፡፡

በበኩላችንም አመልካች መጋቢት 5 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሠረት በማድረግ ክርክሩ ሰምተናል፡፡ አቤቱታው በሰበር ችሎት እንዲታይ የተወሰነው አመልካች የወሰደው የስራ ውለ የማቋረጥ እርምጃ በይርጋ የታገደ ነው የመባሉን አግባብነት ለመመርመር ነው፡፡ በዚህ መሠረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ብይን እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል፡፡

እንደምንመለከተው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከአመልካች የቀረበውን የስረ ነገር ክርክር አልሰማም፡፡ ባጭሩ ብይኑን የሰጠው የተጠሪ የሥራ ውል የተቋረጠው ለውሉ መቋረጥ ምክንያት ነው የተባለው ድርጊት /ጥፋት/ ከተፈጸመ አንድ ወር ካለፈ በኋላ በመሆኑ በይርጋ ታግዶአል በማለት ነው፡፡ በሆኑም በአሁኑ ደረጃ ለመመርመርና ውሣኔ ለሰጠው የሚገባው ነጥብ በእርግጥ ለክርክሩ አወሳሰንበዋቢነት የተጠቀሰው የአዋጅ ቁ. 337/96 አንቀጽ 27/3/ የሚለው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤተ እንደሚለው ነው ወይ የሚለው ነው፡፡ ከዚህም ጋር በማያያዝ ድርጊቱ በተፈጸመበት እና አመልካች የሥራ ውል የማቋረጥ እርምጃ በወሰደበት መሃከል ያለው ጊዘ ምን ያሕል ነው የሚለውን የፍሮ ነገር ሁኔታም መታየት ያለበት ነው፡፡

ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር በተለይ ደግሞ አቤቱታ ከቀረበበት ብይን ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው ተጠሪ ጥፋቱን /ድርጊቱን/ ፈጸመ የተባለው መስከረም 24 እና 25 ቀን 99 ዓ.ም. ሲሆን፣ አመልካች የስሪ ውል የማቋረጥ እርምጃ የወሰደው ጥቅምት 25 ቀን ነው፡፡ ይህ እንግዲህ በፍሮ ነገር ረገድ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ሕጉ ለምን ይላል የሚለው ደግመ ቀጥለን እንመልከት የአዋጁ አንቀጽ 27 አሠሪው ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ማቋረጥ የሚችልባቸውን ምክንያቶች /ሁኔታዎች/ በዝርዝር የያዘ ነው፡፡ የዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /3/ም አሠሪው የስራ ውሉን ለማቋረጥ ያለውን መብት በይርጋ የሚቀርብበት ምክንያት ይዞአል፡፡ ይህም የሚሆነው /የስራ ውሉን ለማቋረጥ ያለው መብት ይርጋ ቀሪ የሚሆነው/ ውሉ የሚቋረጥበት ምክንያት መከሰቱን ካወቀበት ከ3ዐ /ሠላሣ/ የሥራ ቀናት በኋላ እንደሆነ በሕጉ በግልጽ ተቀምጦአል፡፡ እዚህ ላይ በሚገባ ሊተኮርበት የሚገባውም “የስራ ቀናት” የሚለው ሐረግ ነው፡፡ በሕጉ አባባል አሠሪው መብቱን በይርጋ የሚያጣው /የሚቀርበት/ ሠላሣ ቀናት ወይም አንድ መሆን አለባቸው፡፡ በያዝነው ጉዳይ እንደምናየው ከመስከረም 24 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 99 ዓ.ም. ድረስ ያለው ጊዜ የሚታሰበው ቢያንስ እሁድነ ጨምሮ ነው፡፡ እሁድ የስራ ቀን አይደለም ለን ብንወስድ አራት እሁዶች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ በዚህ ስሌት መሠረትም አመልካች የስራ ውል የማቋረጥ እርምጃውን የወሰደው ተጠሪ ፈጸመ የተባለውን ድርጊት /ጥፋት/ መከሰቱን ባወቀ በ26ኛው የስራ ቀኑ ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንዳለው የአመልካች መብት በይርጋ የታገደ ወይም ቀሪ የሆነ አይደለም፡፡ ተጠቃሎ ቢታይ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል፡፡ ስለዚህም የሚከተለው ውሣኔ ሰጥተናል፡፡

ው ሣ ኔ

  1. አቤቱታ የቀረበበት በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 25115 ሰኔ 26 ቀን 99 ዓ.ም. ተሰጥቶ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 5768ዐ ጥር 21 ቀን 2ዐዐዐ በሰጠው ትዕዛዝ የፀናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሠረት ተሽሮአል፡፡
  2. አመልካች የስራ ውል የማቋረጥ መብቱ በይርጋ አልታገደበትም ብለናል፡፡ ስለዚህ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር በዚያው መዝገብ እንዲቀጥለ በማድረግ የስራ ውሉ የተቋረጠው በሕግ አግባብ ነው ወይስ ከሕግ ውጪ ነው በሚለው ጭብጥ ላይ ከግራ ቀኝ ወገኖች የሚቀርብለትነ ከከር ከሰማ በኋላ የመሰለውን ውሣኔ ይስጥ በማለት ጉዳዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 341 መሠረት ይመለስለት ብለናል፡፡ ይፃፍ፡፡
  3. ወጪና ኪሣራ በሚመለከተ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ነ/ዓ

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s