ከስልጣን በላይ የሆነ አስተዳደራዊ ውሳኔ በፍርድ ቤት ስለሚታረምበት ሁኔታ


የሰበር መ/ቁ. 45ዐ91

ጥር 27 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም

ዳኞች፡– ተገኔ ጌታነህ

ሐጎስ ወልዱ

ሂሩት መለሰ

ብርሃኑ አመነው

አልማው ወሌ

አመልካች፡– 1. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር – ነገረፈጅ ትውስታ ግዛው ቀረቡ

2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር – ነገረ ፈጅ ትውስታ ግዛው ቀረቡ

3. የካ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ባለሥለጣን – ነገረ- ፈጅ ፍፁም ካሣዬ ቀረቡ፡፡

4. ወ/ሮ ነፃነት አለበል- ወኪል ጌታሁን ታደሰ ቀረቡ

5. አቶ ዘላለም አለበል – ቀረቡ

ተጠሪ፡-1/ ጊፍት ሪል እስቴት ኃ.የተ.የግል ማህበር – ጠበቃ ቴዎድሮስ ምህረት ቀረቡ

2/ ጊፍት ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር         ..       ..        ..

በመ/ቁጥር 45ዐ91፣ 45ዐ92፣ 45ዐ93፣ 45ዐ94፣ የቀረቡት ጉዳዮች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/

ቁጥር 11 መሠረት አጣምረን በመመርመር ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍ ር ድ

ጉዳዩ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በዚሁ ፍርድ ቤት ከሣሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪዎች ናቸው፡፡ የአሁኑ 1ኛ፣2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ደግሞ አመልካwች የነበሩ ሲሆን 4ኛ እና 5ኛ ተጠሪዎች ጣልቃ ገቦች ነበሩ፡፡

የስር ከሣሾች የክስ ይዘት፡- 1ኛ ከሣሽ ከ2ኛ አመልካች ጋር በየካቲት ዐ2 ቀን 1997 ዓ.ም በተፈረመ የከተማ ቦታ ሊዝ ውል እና ነሐሴ 16 ቀን 1998 ዓ.ም በተፈረመ ማሻሻያ ጠቅላላ ስፋቱ  162,996.6 ካሬ ሜትር ቦታ በየካ ክፍለ ከተማ ለሪል እስቴት አገልግሎት ለማዋል ቦታውን ተከራይቶ መረከቡን፣ ከተረከበው ከዚህ ቦታ ውስጥ በካርታ ቁጥር 11ዐ6ዐ8 ተረጋግጦ በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 2ዐ/21  ክልል ከተሰጠው ይዞታ ውስጥ ተቀንሶ ለጣልቃ ገቦች እንዲሰጥ የከሣሾች ካርታ በዚሁ መሠረት እንዲስተካከል መወሰኑን፣ 2ኛ አመልካች በቁጥር መልአባ/1736/2ዐዐዐ በ2ዐ/2/2ዐዐዐ ዓ.ም  በፃፈውና ለ3ኛ አመልካች ግልባጭ ካደረገለት ደብዳቤ ለመረዳት የቻሉ መሆኑን፣ 3ኛ አመልካችም ይህንኑ ደብዳቤ መነሻ በማድረግ በቁጥር የካልየ /13/88/ዐዐ ጥቅምት 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ ለጣልቃ ገቦች ይዞታ ተቀንሶ ለ1ኛው ተጠሪ 85,6ዐ9 ካሬ ሜትር ቦታ በካርታ ቁጥር 1ዐ822 የተዘጋጀ ስለሆነ የቀድሞውን ካርታ መልሱ በሚል ትእዛዝ መስጠቱን በመዘርዘር 3ኛ አመልካች ካርታውን ለመቀነስ ከሕግ ውጪ በአንቅስቃሴ ላይ ስለሚገኝ እንዲቆምላቸው ይወስንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው፡፡ የአሁኑ አመልካwች በስር ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርበዋል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ከቀረቡት ነጥቦች መካከል አንዱ ካርታ ለመስጠት ለመሠረዝና ለማስተካከል ሥልጣን የተሰጠው ለከተማው አስተዳደር እንጂ ለፍርድ ቤቶች አለመሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት አስገዳጅ ውሣኔ የሰጠበት በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለውም የሚል ነው፡፡ የስር ፍርድ ቤትም በዚህ ነጥብ ላይ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በዋቢነት በመጥቀስ ጉዳዩ በፍርድ ሊወሰን የሚገባው ሣይሆን በአስተዳደራዊ ውሣኔ የሚያልቅ በመሆኑ ፍርድ ቤት ሊመለከተው የሚችለው አይደለም በማለት የአመልካwችን መከራከሪያ ነጥብ በመቀበል መዝገቡን ዘግቶታል፡፡ ከዚህ በኋላ ተጠሪዎች ይግባኛቸውን ለከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት የካርታ መቀነስ ድርጊቱ በሕግ መሠረት የተፈፀመ መሆን ያለመሆኑን በጭብጥነት ይዞ ለማየት በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41/1/ሀ/ እና /መ/ መሠረት ሥልጣን አለው በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤትን ብይን በመሻር በጉዳዩ ላይ የቀረቡትን  ሌሎች ክርክሮች በመመርመር ተገቢውን ውሣኔ እንዲሰጥበት መልሶለታል፡፡ ከዚህም በኋላ ለከተማው ሰበር ሰሚ ችሎት አመልካwች አቤቱታቸውን አቅርበው ተቀባይነት አላገኙም፡፡ የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ ለማስቀየር ነው፡፡

የ1ኛ እና 2ኛ አመልካwች ነገረፈጅ መጋቢት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፉት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ የ3ኛ አመልካች ነገረፈጅ ሚያዚያ ዐ6 ቀን 2ዐዐ1 በፃፉት ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ፣ 4ኛ አመልካች ሚያዚያ ዐ7 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፉት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ እንዲሁም 5ኛ አመልካች ጠበቃ ሚያዚያ ዐ5 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፉት ስድስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ላይ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚሉበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል፡፡ አቤቱታቸው ተመርምሮም በሊዝ የተሰጠው የቦታ ይዞታ ሊቀነስ አይገባም በማለት ለከተማ ነክ ፍርድ ቤት የቀረበውን የዳኝነት ጥያቄ ፍርድ ቤት ተቀብሎ ለማየት ስልጣን ያለው መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ ተደርጎ ተጠሪዎች የጽሑፍ መልስ አቅርበዋል፡፡ አመልካwችም በተጠሪዎች በተሰጠው መልስ ላይ የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙ ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል፡፡

ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው 1ኛ ተጠሪ ከ2ኛ አመልካች ጋር በየካቲት ዐ2 ቀን 1997 ዓ.ም በተፈረመ የከተማ ቦታ ሊዝ ውል እና ነሐሴ 16 ቀን 1998 ዓ.ም በተፈረመ ማሻሻያ ጠቅላላ ስፋቱ 162,996.6 ካሬ ሜትር ቦታ በየካ ክፍለ ከተማ ለሪል እስቴት አገልግሎት ለማዋል ቦታው ተከራይቶ መረከቡን ከተረከበው ከዚህ ቦታ ውስጥ በካርታ ቁጥር 11ዐ6ዐ8 ተረጋግጦ በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 2ዐ/21 ክልል ከተሰጠው ይዞታ ውስጥ ተቀንሶ ለጣልቃ ገቦች እንዲሰጥ የተጠሪዎች ካርታ በዚሁ መሠረት እንዲስተካከል መወሰኑን፣ 2ኛ አመልካች በቁጥር መልአባ/1736/2ዐዐዐ በ2ዐ/2/2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈውና ለ3ኛ አመልካች ግልባጭ ካደረገለት ደብዳቤ ለመረዳት የቻሉ መሆኑን 3ኛ አመልካችም ይህንኑ ደብዳቤ መነሻ በማድረግ በቁጥር የካልየ/13/88/ዐዐ ጥቅምት 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ የጣልቃ ገቦች ይዞታ ተቀንሶ ለ1ኛው ተጠሪ 85,6ዐ9 ካሬ ሜትር ቦታ በካርታ ቁጥር 1ዐ822 የተዘጋጀ ስለሆነ የቀድሞውን ካርታ መልሱ በሚል ትእዛዝ መስጠቱን ሲሆን ይህም የሚያሣየው ቀደም ብሎ ለ1ኛ ተጠሪ የተሰጠው  የሊዝ ቦታ ካርታው ተሻሽሎ የቦታውን ስፋት ተቀንሶ ለ4ኛ እና 5ኛ ተጠሪዎች የተቀነሰው ቦታ እንዲሰጥ መወሰኑን ነው፡፡ ተጠሪዎች አጥብቀው የሚከራከሩት የ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ አመልካwች እርምጃ ሕገወጥ ነው በሚል ነው፡፡ አመልካwች በበኩላቸው የክፍለ ከተማው አስተዳደር ካርታ መስጠት፣ የመሠረዝ፣   የማሻሻል፣ የማምከን፣ የማገድ እና አሻሽሎ የመስጠት ሙሉ ስልጣን በሕግ ተሰጥቶታል፡፡ የፌዴራሉ ሰበር ችሎትም በመ/ቁጥር 276ዐ4 ካርታ የመስጠት ስልጣን የአስተዳደር የስራ ተግባር መሆኑን በመዘርዘር አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል በሚል ተከራክረዋል፡፡

በመሠረቱ ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት  ሥልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሣኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድሪ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 37/1/  ድንጋጌ በግልጽ የሚያሣየው ጉዳይ ነው፡፡ ከዚሁ የሕገ መንግሥት ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ፍርድ ቤቶች አንድ ጉዳይ /አቤቱታ/   ተቀብለው ውሣኔ መስጠት የሚችሉት ዳኝነት የተጠየቀበት ጉዳይ በሕግ ለሌላ አካል ያልተሰጠ ጉዳይ በሚሆንበት ጊዜ እንደሆነ መሆኑን ነው፡፡ በሕግ ተለይተው በአስተዳደራዊ ውሣኔ እንዲቋጩ በተባሉ ጉዳዮች ላይ መደበኛ ፍርድ ቤት የመዳኘት የስረ ነገር ስልጣን ስለሌለው በሕጉ መሠረት አንድ አስተዳደር አካል ቀርቦ አስተዳደራዊ ውሣኔ የተሰጠበትን ጉዳይ ወይም ለአስተዳደር መቅረብ የሚገባውን ጉዳይ ፍርድ ቤት ሊያስተናግደውም ሆነ አከራክሮ ውሣኔ ሊሰጥበት አይችልም፡፡ ለአንዳንድ የመንግሥት አካላት በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ  የመወሰን ስልጣን የሚሰጡት ሕጎች መጠበቅና መከበር ያለባቸው ሲሆን የዳኝነት አካል ስልጣንም በሕግ የተወሰነ ስለሆነ ሕግ የመተርጎም ስራው በሕጉ በተመለከተው አድማስ የሚመራ ይሆናል፡፡ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 4 ድንጋጌ የሚያሣየውም ፍርድ ቤቶች በሌላ ሕግ በግልጽ በታገዱ ጉዳዮች ላይ አከራክሮ የመወሰን ስልጣን የሌላቸው መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም በአስተዳደራዊ ውሣኔ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኙ በሕግ ተለይተው የተቀመጡ ጉዳዩችን ፍርድ ቤቶች የመዳኘት ስልጣን የሌላቸው መሆኑ ሊስተዋል የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡

ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም የተጠሪዎች የዳኝነት ጥያቄ /ክርክር/ መሠረት ያደረገው ከ2ኛ አመልካች ጋር ባደረገው የሊዝ ውል የተሰጠውን ቦታ ስፋት ከሕግ ውጪ ተቀንሶ ካርታውም በዚሁ እንዲስተካከል መደረጉ ያላግባብ ነው የሚል ነው፡፡ በዚህ መልኩ የሚቀርበውን የዳኝነት ጥያቄ የክፍለ ከተማው አስተዳደር በሚሰጠው አስተዳደራዊ ውሣኔ የመጨረሻ እልባት የሚሰጥበት መሆኑን ወይም ጉደዩ በመደበኛ ፍርድ ቤት ሊታይ የማይገባው መሆኑን የሚደነግግ ሕግ የለም፡፡ የከተማው አስተዳደር ካርታ የመስጠት የመሠረዝ፣ የማሻሻል፣ የማምከን፣ የማገድ እና አሻሽሎ የመስጠት ሙሉ ስልጣን ያለው ቢሆንም የሊዝ ውልን መሠረት አድርጎ የተሰጠውን ካርታ መልሶ ከሕግ ውጩ ቀንሶ ሲገኝ በእርምጃው ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ጉዳዩን ለፍርድ ቤት እንዳያቀርብ የሚከለከልበት ስርዓት የሌለ ስለመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት ስልጣንና ኃላፊነት ለመደንገግ የወጣው፣ ክርክሩ ሲጀመርም ሆነ ከተጀመረ በኋላ በስራ ላይ ያለው ሕግ ያሣያል፡፡ ይልቁንም የተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41/1/ሀ/ እና/መ/ ድንጋጌዎች ሲታዩ የተያዘውን ጉዳይ አይነት የአዲስ አበባ ከተማነክ ፍርድ ቤት ተቀብሎና አከራክሮ ለመወሰን የስረ ነገር ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ ያስገነዝባሉ፡፡ አመልካች ይህ ሰበር ችሎት አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጠ በማለት የሚጠቅሱት መ/ቁጥር 276ዐ4 በተያዘው ጉዳይ ካለው ፍሬ ነገር እና የሕግ ክርክር ሙሉ በሙሉ ግንኙነት አለው ሊባል የሚችል አይደለም፡፡ በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበው የአመልካwች ክርክር ተቀባይነት ያለው ሁኖ አልተገኘም፡፡ ስለሆነም የተጠሪዎች ጥያቄ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ከሕግ ውጪ በሊዝ የተወሰደ ቦታ ስፋት በመቀነስ ካርታ አሻሽሎ ይህንንም እንዲያርም ጠይቀን ፈቃደኛ አልሆነም በማለት በሊዝ ውል ያገኙት የንብረት መብታቸው /የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 4ዐ/6/ ይመለከቷል/ በፍርድ እንዲጠበቅላቸው የሚጠይቅ በመሆኑ በፍርድ ቤት ሊያስተናግድ የሚገባው እና ውሣኔ የሚሰጥበት ጉዳይ በመሆኑ የአዲስ አባ ከተማ ነክ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የከተማው መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ መሻሩም ሆነ የሰበር ችሎቱ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ማጽናቱ ከአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41/1/ሀ/ እና /መ/ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ አንፃር ሕጋዊ ሆኖ አግኝተናል፡፡ በዚህ ምክንያት በውሣኔው ላይ የተፈፀመ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስነናል፡፡

ው ሣ ኔ

1.                    በአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር ዐ6721 ታህሣሥ ዐ7 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ተሰጥቶ በከተማው ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር ዐ9ዐ95 መጋቢት 18 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሠረት ፀንቷል፡፡

2.                    በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ተ.ወ

1 Comment

  1. Aman says:

    Dear Mr. Abrham, I am so proud of your work and achievement in compiling and making the Ethiopian laws, cases and other materials in such an easy way. We have been sitting on our hands while there was a strongly felt need for such kind of website and you deserve appreciation for such work. Kudos! I say to you. I hope you continue with the hard work and develop the website further. I have already downloaded my first proclamation and I have experienced how easy it is to access the documents. Thank you!

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s