- በእርግጥ መልካም ምግባር ተጠብቆ እንዲቆይ ሕግ አስፈላጊ ነው፡፡ ሕግ ፀንቶ እንዲቆይም ግን መልካም ምግባር የግድ አስፈላጊ ነው፡፡
ኒኮሎ ማኪያቬሊ
- የጡንቻ ድንፋታና የመሣሪያ ኳኳታ ባየለበት የሕግ ድምጿ አይሰማም፡፡ ስትናገር በለሆሳስ ነውና፡፡
ጌየስ ማረየስ
- እኔ አንዲት አገር በመልካም ሁኔታ እየተመራች ነው የምለው ሕጐቿ ጥቂት ሆነው ግን የምር (በጥብቅ) ተፈፃሚነት ሲኖራቸው ነው፡፡
ሬኔ ዲካርተስ
- ሰዎች ንፁሐን (ቅዱሳን) ከሆኑ ሕግ ረብየለሸ ነው፡፡ ሰዎች ከረከሱ (ኀጢአተኛ ከሆኑ) ደግሞ ሕግ መጣሱ አይቀርም፡፡
ቤንጃሚን ዲዜራሊ
- ሕግ ብቻውን ሓሳብን በነፃ የመግለፅ መብት መከበር ዋስትና አይሆንም፡፡ እያንዳንዱ ሰው ሓሳቡን በነፃነት ያለገደብ እንዲገልፅ በመላው ሕዝብ ዘንድ የመቻቻል መንፈስ መስፈን አለበት፡፡
አልበርት አነስታይን
- በአንድ አገር መንግስት ውስጥ ወንጀልን ለመከላከል የሚወጡት ጥቂት ሕጐች ራሳቸው ቀንደኛ ወንጀለኛ ሆነው ይገኛሉ፡፡
ፍሬደሪክ ኤንግልስ
- ረሃብ ሲኖር ሕግ አይከበርም ሕግ ሳይከበር ሲቀር ደግሞ ረሃብ ይኖራል፡፡
ቤንጃሚን ፍራንክሊን
- ሕግ ደሃውን ሲፈጨው ሃብታም ሕጉን ያስፈጨዋል፡፡
ኦሊቨር ጉልድስሚዝ
- ፍትሕ ሕያው የሚሆነው በሕግ በቅርፅ ሳይሆን በመንፈሱ ነው፡፡
አርል ዋረን
- ሕግ ከመብዛቱ የተነሳ ሊነበብ አዳጋች ከሆነ ካለመጣጣሙ የተነሣ በሚገባ ሊታወቅ ካልቻለ ሕጉ የወጣው ሕዝቡ በመረጣቸው ሰዎች መሆኑ ለሕዝቡ የሚፈይደው ነገር የለም፡፡
አሌክሳንደር ሃሚልተን
- አፍቃሬ ሙግት የሆኑት ጠበቃዎቻችን ሲበዛ ተከራካሪና እረፍት የለሸ መሆናቸውን ሳስብ በሚቀጥለውም ዓለም ሳይቀር በሲኦል ውስጥ ለደንበኞቻቸው የሚሟገቱ ይመስለኛል፡፡
ሮበርት በርተን