መስቀለኛ መዘዝ


የተከሳሽ ተከላካይ ጠበቃ ምንም ላይፈይድለት ነገር ምስክሯን  ‘እማማ እኔን ያውቁኛል?’ ሲል ይጠይቃቸዋል

ምስክር — ‘ እንዴት አላውቅህም አንተ ሞላጫ! አውቅሃለው እንጂ !ከልጅነትህ ጀምሮ አሳምሬ አውቅሃለው የሌባ ዐይነ ደረቅ! ደሞ  አፍህን ሞልተህ ያውቁኛል ወይ ትላለህ?’

ጠበቃው በመቀጠል ‘ ዐቃቤ ህጉንስ ያውቁታል?’  ሲል ጠየቃቸው

ምስክር — ‘እንዴት አላውቀው?! ይሄ ወስላታ! አተራማሽ!  ሚስትና ልጆቹን ቤት ጎልቶ ሴት ሲያሳድድ ነው እኮ የሚውለው እሱንማ እኔ ብቻ ሳልሆን አገሩ በሙዑ ያውቀዋል’

በመቀጠል የነገሩ አካሄድ ያሰጋቸው ክቡር ዳኛ በፍጥነት በምስክርነቱ መሃል በመግባት ጠበቃውና ዐቃቤ ህጉ ወደሳቸው ዘንድ እንዲመጡ በእጃቸው ምልክት ከሰጡ በኋላ ‘ሁለታችሁም ወደዚህ ቅረቡ’ በማለት ጠንክር ያለ ትዕዛዝ ሰጡ ሁለቱም እንድተባሉት የተከበሩት ዳኛ ፊት ተጠግተው ቆሙ

ዳኛው ሁለቱንም ገልመጥ ገልመጥ  አድርገው ተመለከቱና  ‘ አንተም ሆንክ አንተ! አንድሽም የኔን ስም ታነሺና! ወዮልሽ! በችሎት መድፈር ወንጀል ልክሽን ነው የማከናንብሽ ‘

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s