ማመልከቻ ፃፍ


ማመልከቻ ሳልፅፍ ከአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት የማገኘው ነገር ቢኖር ያው የፈረደባት ያችኑ ደመወዜን ብቻ ነው  ሌላ ሌላውን ቢያስፈልግም ባያስፈልግም ማመልከቻ መፃፍ ግድ ይላል  ምንም እንኳን ከማመልክቻው ለጥቆ በአራት ምስክር ፊት የፅሁፍ ውል የምገባ ቢሆንም ከዚያም አልፎ ስፍር ቁጥር በሌላቸው ሰነዶች ውስጥ ፊርማዬን የማኖር ቢሆንም መጀመሪያ ይህንኑ ገልጬ ይኸው እንዲፈጠምልኝ መለመን አለብኝ

ልመናዬም በታላቅ ትህትናና በማክበር መታጅብ ይኖርበታል  ” እኔ ስሜ ከላይ የተጠቀሰው  ውሃ….. መብራት…..ስልክ….. ስለምፈልግ  እንዲገባልኝ ስል በታላቅ ትህትና እጠይቃለው”  አንዳንዴ አንጀት ለመብላት ገና ምኑም ሳይጀመር ” ለሚደረግልኝ ትብብር ከወዲሁ በቅድሚያ አመሰግናለሁ!” የሚል ማሳረጊያ ተጨማሪ ነጥብ ሊያሰጥ ይችላል    ምስጋናው ቀብድ መሆኑ ነው

አንድ ሰው የመንግስት አገልግሎት ሲጠይቅ በወጉ ቅፅ ላይ ዝርዝር መረጃ ሰጥቶ በፊርማው ሃሳቡን እስከገለፀ ድረስ ለምን ያመለክታል? ማመልክት ማለትስ ምንድነው ?ባያመለክትስ?

ሁሉም ማመልከቻ ፃፍ ባይ ነው  ወህኒ የሚወርድ እስረኛስ ሳይጠየቅ ይቀራል? ” እኔ ስሜ ከዚህ በላይ (ወይም ከዚህ በታች) የተገለፀው በሰራሁት ወንጅል ጥፋተኛ ተብዬ የተፈረደብኝ ስለሆነ እናንተ ዘንድ ቀርቤ የእስር ጊዜዬን እንዳጠናቅቅ እንዲፈቀድልኝ በታላቅ አክብሮት እየጠቅኩ በቆይታይ ለሚደረግልኝ ትብብር ሁሉ ከወዲሁ አመሰግናለሁ”

ማመልከቻው ተፃፈ  ሆኖም ነገሩ በዚህ አይቋጭም የማመልከቻ አዋቂ ነኝ የሚል ‘የማመልከቻ ኤዲተር’  የተለያዩ የቴክኒክ ችግሮችን እየመዘዘ ቢያንስ አንድ ጊዜ ይመልስባችኋል  “ውሃ ይግባኝ” የሚል ማመልከቻችሁን ከ20 ደቂቃ በላይ መነፅሩን እያወለቀ እየሰካ ለፈተና የሚዘጋጅ ይመስል ትኩር ብሎ ያነበዋል ስህተት ሲያጣ ፊቱን ያጨማድዳል ድንገት ፈገግ ይላል በልቡ “ተገኘሽ!” እያለ

ከፈገግታው ቀጥሎ ……………………………………………………………

” እም……! ማመልከቻው ግልፅ አይደለም  ውሃ ይግባልኝ ብለው ነው ያመለከቱት   የምን ውሃ ነው የሚገባልዎት? የዝናብ ውሃ ነው? የቧንቧ ውሃ ነው? እሽግ ውሃ ነው ? ምን ዓይነት ውሃ እናስገባልዎት?  ይህንን ግልፅ አድርገው ማመልከቻውን እንደገና ይፃፉ!”

 

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s