በእግዚአብሔርና በሰይጣን ላይ የቀረቡ ክሶች


የሰው ልጅ ከእንስሳት የሚለይበት ዐቢይ ነጥብ ከሳሽነቱ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም (ሊሆንም ይችላል) ሰው ከሳሽ ፍጡር ነው የክሱና የከሳሹ ብዛት ብቻ ሳይሆን የክሱ ዓይነትና ይዘት ሰዎች ከሙግት ጋር ስላላቸው ጥብቅ ቁርኝት አስረጂ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል

በዓለማችን ላይ እጅግ በጣም በርካታ ፌዝ መሳይ ክሶች ቢኖሩም በእግዚአብሔርና በሰይጣን ላይ የቀረቡት ክሶች ግን በአውራነት ሊፈረጁ ይችላሉ ነገሩ የፌዝ ቢመስልም ከሳኞቹ ግን የፌዝ አይደሉም ለምሳሌ በእግዚአብሔር ላይ የክስ አቤቱታ አዘጋጅቶ ፋይል ያስከፈተው ግለሰብ አንቱ የተባለ የአሜሪካ ኔብራስካ ግዛት ሴናተር ነው ግለሰቡ ኤርኒ  ቻምበርስ ይባላል (Ernie Chambers) ይባላል ይህ ሰው በኤሜሪካ ዳግላስ ካውንቲ ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ በእግዚአብሔር ላይ ቋሚ የዕግድ ትዕዛዝ እንዲሰጠው ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን በእግዚአብሔር ተፈጸሙ ያላቸውን በደሎችንም በክሱ ላይ  ዘርዝሯል ጉዳዩን ያዩትዳኛ የቀረበውን ክስ በጥሞና ከመረመሩ በኋላ “እግዚአብሔርን በአድራሻው ፈልጎ መጥሪያውን ማድረስ ስለማይቻል” በሚል ምክንያት ክሱን ውድቅ አድርገውታል

 

ከሳሹ ሴናተር ኤርኒ ቻምበርስ

 

 

በሰይጣን ላይ የቀረበው ክስ እ ኤ አ 1971 ዓ ም የቀረበ ሲሆን ከሳሹም ጌራልድ ማዮ Gerald Mayoይባላል ከሳሽ በሰይጣንና ጀሌዎቹ ላይ ባቀረበው በዚሁ ክስ ሰይጣንና ጭፍራዎቹ ህገ መንግስታዊና ሰብዓው መብቶቹን በመጣስ በተደጋጋሚ አላስገባ አላስወጣ ብለው ነፃነቱን ና የመኖር መብቱን እንዳሳጡት በምሬት በመግለፅ ክቡር ፍርድ ቤቱ የዕግድ ትዕዛዝ ይሰጠው ዘንድ ተማፅኗል

ጉዳዩን የመረመሩት ዳኛ ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ ያደረጉት ቢሆንም በውሳኔያቸው ላይ ክሱን በቀላሉ አጣጥለው መዝገቡን ለመዝጋት አለፈለጉም እያንዳንዱ ነጥብ እየተነሳ ከግራም ከቀኝም እየተዳሰሰ መዝገቡ በጥልቀት ተመርምሯል

በአጭሩ ለማስቀመጥ ፍርድ ቤቱ በሰይጣን ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ ሲያደርግ የሚከተኩትን ዐቢይ ምክንያቶች በማተት ነበር

  • የክስ ምክንያት የከሳሽ መብት በእርግጥ ተረግጧል ቢባል እንኳን ፍርድ ቤቱ ሊያደርግ የሚችለው ማለትም ሊሰጠው የሚችለው መፍትሄ የለም ፍርድ ቤት ሰይጣንን ምን ሊያደርገው ይችላል?
  • የተከሳሽ አድራሻ ክሱ ይቅረብ ቢባል እንኳን ለሰይጣን መጥርያ እንዴት ይደርሰዋል?
  • የቡድን ክስ ሰይጣን የጀሌዎቹን ማለትም የጭፍሮቹን ጥቅም ሊያስጠብቅ እንደሚችል ሳይረጋገጥ ክሱን በዚህ መልኩ ማስኬድ አስቸጋሪ ነው በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ውክልና ያለው ስለመሆኑም አልተረጋገጠም
  • ፍትሃዊነሐት ተከሳሾች ችሎት ቢመጡ መጀመሪያ የሚያዩት ከዳኛው አናት ላይ  “In God We Trust” የሚል በትልቁ የተፃፈ ፅሁፍ ነው በዚህ ሁኔታ ተከሳሾች ፍትሃዊ ዳኝነት ያገኛሉ ተብሎ አይገመትም

“ስለሆነም የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርገነዋል   መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ    የይግባኝ መብት የተጠበቀ ነው”

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s