ሕግ ነክ ጥቅሶች #2


  • ሕግ መመዘን ያለበት በተገቢው መንገድ ቢፈጸም በሚያስገኘው ጥቅም ብቻ ሳይሆን በተዛባ ሁኔታ ቢፈጸም ሊያስከት ከሚችለው ኪሳራና ጉዳት አንፃር ጭምር ነው፡፡

ሊንደን  ቤንስ ጆንሰን

  • ጥሩ ጠበቃ ጥሩ የሽያጭ ሠራተኛ ነው

ጃኔት ሮኖ

  • ሕገ – መንግስት በስም ሳይሆን በገሃድ ያለ ነገር ነው፡፡ ህላዌነቱ ሃሳባዊ ሳይሆን ተጨባጭነት አለው፡፡ ሊታይ፣ ሊዳሰስ፣ ሊጨበጥ ካልቻለ የለም ማለት ነው፡፡ ሕገ መንግስት የመንግስት ውጤት አይደለም፡፡ ይልቅስ ከመንግስት ቀድሞ ያለ የመንግስት መሠረቱ ሕገ መንግስት ነው፡፡ የአንድ አገር ሕገ መንግስት መንግስቱን የሚያቋቁሙት ህዝቦች ነፃፈቃድ ውጤት ነው፡፡

ቶማስ ፔይን

  • ጠብመንጃና ህግ አንድ ላይ አይበቅሉም፡፡

ጁሊያን ቄሳር

  • በልብ ውስጥ ክፋት ካለ አይንና ጆሮ ውሸታም ምስክሮች ናቸው፡፡

ሄራክላተስ

  • ጠበቃ ቦርሳውን ብቻ ይዞ አንድ መቶ ጠብመንጃ ከያዙ ሰዎች የበለጠ መስረቅ ይችላል፡፡

ማሪዮ ፑዞ

  • ዳኛው ሽጉጥ መታጠቅ ሲጀምር ፍርድ ቤቶች መዘጋት አለባቸው፡፡

ስቴፈን ጀጆንሰን ፊልድ – ዳኛ (መሳሪያ እንዲታቅ ሲጠየቅ የሰጠው መልስ)

  • ከተፈጥሮ ህግ የበለጠ ሌላ ቅዱስ ህግ አላውቅም፡፡

ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን

  • በእርግጥ መልካም ምግባር ተጠብቆ እንዲቆይ ህግ አስፈላጊ ነው፡፡ ህግ ጸንቶ እንዲቆይም ግን መልካም ምግባር የግድ አስፈላጊ ነው፡፡

ኒኮሎ ማኪያቬሌ

  • የጡንቻ ድንፋታና የመሳሪያ ኳኳታ ባየለበት የህግ ድምጻ* አይሰማም፡፡ ስትናገር በለሆሳስ ነውና፡፡

ጌየስ ማረየስ

 

 

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s