የተከበረችዋ ፍርድ ቤቷ!


በየትም አገር ቢሆን ፍርድ ቤት ይከበራል፡፡ ይህ የፍርድ ቤት ክብር ጉዳይ ለብዙ ሰዎች ምቾት አይሰጣቸውም፡፡ በተለይ በኛ ሀገር አብዛኛው ሰው የፍርድ ቤት ክብርን የሚያይዘው ከፍርሀት ጋር ነው፡፡ ሆኖም ፍርድ ቤቱ በወጉና በስርዓቱ ዳኝነቱን እንዲያከናውን ሊከበር እንጂ ሊፈራ አይገባውም፡፡ ይኸው የፍርድ ቤት ክብር ተምሳሌታዊ በሆነ መልኩ ከሚገለጽበቸው መንገዶች አንዱ በክርክር ወቅት ፍርድ ቤት የሚጠራበት የአክብሮት ስያሜ ነው፡፡ በብዙ አገራት my lord! Your honor! እያሉ መጥራት የተለመደ ነው፡፡ በአገራችንም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጌታዬ! እያሉ ሙግት መጀመር እንዲሁ የተለመደ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት በጣም ተቀባይነት ያገኘው አጠራር ‹‹ክቡር ፍርድ ቤት›› ወይም ‹‹የተከበረው ፍርድ ቤት›› የሚል ነው፡፡ አንዳንድ ባለጉዳዮች ‹‹ክቡር ዳኛ!›› ‹‹ክብርት ዳኛ!›› ማለት ቢያዘወትሩም ይህ አጠራር ግን ለክቡር ዳኞቻችን ብዙም አይመቻቸውም፡፡ አንዳንድ ግብረ-ገብነት ያልገባው ባለጉዳይ ደግሞ ‹‹ አንተ ›› ወይም ‹‹አንቺ›› የሚልበት አጋጣሚ ቢኖርም ይህ አጠራር ግን ለዳኞች ፈጣን ተግሳፅ ይዳርጋል፡፡

በአንድ ወቅት ስለ ፍርድ ቤቱ አጠራር ግራ የተጋባ የሐረርጌ ሰው ከአንድ ሴት ዳኛ ፊት ይቀርባል፡፡ ዳኛዋ በዕድሜ በጣም ወጣት ሲሆኑ አለሳበሳቸውም (አጭር ጉርድ ቀሚስ!) ለእርስዎ አይመችም፡፡ እናም ክቡር ፍርድ ቤት የሚለው አገላለፅ ለተባዕታይ ፆታ መስሎት ‹‹ የተከበረችዋ ፍርድ ቤትዋ!›› በማለት ክርክሩን ጀምሯል፡፡

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s