ቲማቲም አትክልት ነው ወይስ ፍራፍሬ?


አንዳንዴ በተለመደው ዕለታዊ የኑሮ እንቅስቃሴ ቀላል ግምት የሚሰጣቸው አከራካሪ ጉዳዮች በፍርድ ቤት ጭብጥ ሆነው ሲቀርቡ መሰረታዊ በሆኑ የግል እና የንብረት መብቶች ላይ ትልቅ ልዩነት ያመጣሉ፡፡

አሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደረስ የደረሰ አንድ ጉዳይ ቲማቲም አትክልት ነው ወይስ ፍራፍሬ? የሚለው ጥያቄ የክርክሩ ዋነኛ መሠረታዊ ጭብጥ ሆኖ ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ እ.አ.አ በ1883 ዓ.ም. የወጣው የታሪፍ ህግ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ አትክልቶች ላይ የ10 ፐርሰንት ቀረጥ ሲጥል ፍራፍሬ ግን በነፃ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ይፈቅዳል፡፡ የኒዮርክ ከተማ ግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ቲማቲም አትክልት ነው በማለት የቲማቲም አስመጪዎች በሙሉ ግብር እንዲከፍሉ ያስገድዳቸዋል፡፡ ቲማቲም ፍራፍሬ ነው በማለት ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩት የቲማቲም አስመጪዎች ቀረጥ ልንከፍል አይገባም በማለት ክሳቸውን በስር ፍርድ ቤት አቀረቡና ጉዳዩ እያለ እያለ የመጨረሻው የአሜሪካ ፍርድ ቤት ወደሆነው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደረሰ፡፡ ፍርድ ቤቱም ነገሩን በጥሞና ከመረመረ በኋላ በሰጠው ውሳኔ ምንም እንኳን የስነ – ዕፅዋት ባለሙያዎች ቲማቲምን እንደ ፍራፍሬ ቢቆጥሩትም በዋና ምግብነት (ለምግብ መስሪያነት) የሚያገለግልና ሐረግ መሰል ተክል ላይ የሚያድግ ነው፡፡ በማለት ካተተ በኋላ ቲማቲም አትክል ነው፡ በማለት ይግባኙን ውድቅ አድርጎታል፡፡

2 Comments

  1. Abdulfettah says:

    wow it is beuryful

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s