የሚከተሉት ጥያቄዎች በእርግጥ በፍ/ቤት የተጠየቁ ናቸው፡፡ የጥያቄዎቹ አስቂኝነት ሲታይ ጠበቃው በዛን ሰዓት ምን እሰበ ነበር? ያስብላል፡፡ ከጥያቄዎቹ ባሻገር ግራ በተጋቡ ምስክሮች የሚሰጡት መልሶች ትኩረት ሳቢ ናቸው፡፡
ጥያቄ – ከሟች ጋት ትተዋወቃላችሁ?
መልስ – አዎ እንተዋወቃለን፡፡
ጥያቄ – ከመሞቱ በፊት ወይም በኋላ?
ጥያቄ – ውሻውን በጆሮዎቹ ይዞ ወደላይ አንስቶል?
መልስ – አላነሳውም፡፡
ጥያቄ – እሺ የውሻውን ጆሮዎች ምን ሲያደርጋቸው ነበር?
መልስ – አየር ላይ ወደላይ እያነሳቸው፡፡
ጥያቄ – በዛን ጊዜ ውሻው የት ነበር?
መልስ – ጆሮዎቹ ላይ ተጣብቆ?
ጥያቄ – አንተ ከቆምክበት ቦታ ላይ ሆነህ እሱ ይታህ ነበር?
መልስ – አዎ ጭንቅላቱ ይታየኝ ነበር፡፡
ጥያቄ – ጭንቅላቱ የት ነበር?
መልስ – ከትከሻው በላይ፡፡
ጥያቄ – የሽንት ናሙና ለመስጠጥ ብቁ ነህ?
መልስ – እንዴታ ለዛውም ከልጅነቴ ጀምሮ
ጥያቄ – እሺ ወ/ሮ ሱዛን የመጀመሪያው ጋብቻሽ የፈረሰው በምን ምክንያት ነበር?
መልስ – በሞት
ጥያቄ – በማን ሞት?
ጥያቄ – በስራ ላይ መጠጥ ትጠጣለህ?
መልስ – አረ በፍፁም! ጠጥቼ ወደስራ ካልመጣሁ በስተቀር ስራ ላይ ሆኜ አልጠጣም፡፡