በፊሸር እና ሎው (Fisher Vs. Lowe) መዝገብ ከሳሽ በአሜሪካ ሚቺጋን የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበ ክስ ተከሳሹ መኪናውን እየነዳ የከሳሽን የዋርካ ዛፍ ገጭቶ ጉዳት ስላደረሰ ካሳ እንዲከፈለው የሚጠይቅ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ታዲያ ክሱን ውድቅ ያደርግና ተከሳሽን በነፃ ያሰናብተዋል፡፡ በጣም በሚወደው ዛፍ ላይ ጉዳት መድረሱ ያንገበገበው ከሳሽ ግን ፍትህ ተጓድሏል! በሚል በውሳኔው ቅር ተሰኝቶ ይግባኙን ለበላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱም በተመሳሳይ ይግባኙን ውድቅ አድርጎ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማፅናት በድጋሚ ተከሳሹን በነፃ አሰናብቶታል፡፡ ክሱ ከጅምሩ ሲታይ በዛፍ ላይ ጉዳት ደረሰ በሚል ለፍርድ ቤት ጥያቄ መቅረቡ በራሱ ትንሽ አስገራሚ ነው፡፡ የበለጠ የሚገርመው ግን ይግባኝ ሰሚውፍርድ ቤት ውሳኔውን የሰጠው በግጥም መሆኑ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ በግጥም የሰጠው ውሳኔ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
We thought that we would never see
A suit to compensate a tree
A suit whose claim in tort is prest
Upon a mangles tree’s behest;
A tree whose battered trunk was prest
Against a Chevy’s crumples crest;
A tree that faces each new day
With bark and limb in disarray;
A tree that may forever bear
A lasting need for tender care
Flora lovers though we three,
We must uphold the court’s decree.
Affirmed