እውነተኛ የፍርድ ቤት ጥያቄና መልሶች
ጥያቄ – ዶክተር!የሬሳ ምርመራውን ከማድረግህ በፊት የልብ ምት መኖር አለመኖሩን አረጋግጠሃል?
መልስ – አላረጋገጥኩም፡፡
ጥያቄ – ትንፋሽ መኖሩን አለመኖሩን አረጋግጠሃል?
መልስ – አላረጋገጥኩም፡፡
ጥያቄ – ስለዚህ የሬሳ ምርመራውን ስትጀምር በሽተኛው በህይወት ነበር ለማለት ይቻላላ?
መልስ – አይቻልም፡፡
ጥያቄ – እንዴት እርግጠኛ መሆን ትችላለህ? ዶክተር?
መልስ – ምክንያቱም አንጎሉ አጠገቤ ከነበረው ብርጭቆ ውስጥ ነበር፡፡
ጥያቄ – ግን እንደዛም ሆኖ በሽተኛው በህይወት የነበረ ሊሆን አይችልም?
መልስ – ኧረ ይችላል! ምናልባት በዛን ጊዜ የሆነ ቦታ ጠበቃ ሆኖ እየሰራ ይሆናል!፡፡
***********
ጥያቄ – ጥሩ ዶክተር! እንግዲህ አንድ ሰው ባንቀላፋበት በዛው ሲሞት ጸጥ ብሎ ያሸልብና እስከሚቀጥለው ጠዋት ድረስ የሆነውን አያውቅም፡፡ እውነት ነው?
**************
ጥያቄ – የሚ/ር ሃንቲንግተንን ሬሳ የመረመርክበትን ሰዓት በግምት ታውቀዋለህ?
መልስ – የሬሳ ምርመራው በ11፡30 ላይ ተጀመረ ወደ ማታ አካባቢ ነበር፡፡
ጥያቄ – በዛን ሰዓት ሚ/ር ሃንቲንግተን ሞቶ ነበር?
መልሰ – አይ! የኔ ደንቆሮ! ተጋድሞ ለምን የሬሳ ምርመራ እንደማደርግለት ተገርሞ እያየኝ ነበር፡፡
**************
ጥያቄ – ይህ መድኃኒት የማስታወስ ችሎታህን ቀንሶታል?
መልስ – አዎ
ጥያቄ – እንዴት እንደቀነሰው እስቲ ንገረን?
መልስ – ብዙ ነገር እረሳለሁ
ጥያቄ – ትረሳለህ!? እስቲ ከረሳሃቸው ነገሮች መካከል አንዱን ንገረን?
**************
ጥያቄ – ሚ/ር ስሌተር! የተንደላቀቀ የጫጉላ ሽርሽር ላይ ነበርክ፡፡ ልክ ነኝ?
መልስ – አዎ ልክ ነው፡፡ በአውሮፓ አገራት ተዘዋውሬአለሁ፡፡
ጥያቄ – ለመሆኑ አዲሷን ሚስትህን ይዘሃት ነበር የምትዞረው?
*************
ጥያቄ – ዕቃው ምን እንደሆነ ወይም ምን እንደሚመስል አላውቅም ብለሃል፡፡ ግን ግን ቢያንስ ልትገልጸው ትችላለህ?