በአንድ ከፍተኛ ትኩረት በሳበ የሙስና ወንጀል ክስ ጉዳይ ጠበቃው ምስክሩን የመስቀለኛ ጥያቄ ውርጅብኝ ያወርድባቸዋል፡፡ ምስክሩ ትልቅ ሰው ስለሆኑ ጠበቃው በአንቱታ ጥያቄውን ይጠይቃል፡፡
“በዚህ ጉዳይ ላይ በጥቅም ተደልለው 5,000 ብር ጉቦ ተቀብለዋል፡፡ እውነት ነው?” ምስክሩ ግን ጥያቄውን ያልሰሙ በመምሰል ዝም ብለው ወደ ዳኛው አቅጣጭ መስኮት መስኮቱን ማየት ጀመሩ፡፡
“5,000 ብር ጉቦ አልተቀበሉም ወይ!?ይመልሱ እንጂ!” ምስክሩ አሁንም እንደ በፊቱ ወደ መስኮቱ እያዩ ምላሽ ሳይሰጡ ቀሩ፡፡ በዚህ ጊዜ ዳኛው ጣልቃ በመግባት “እባክዎት ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ይስጡ?” በማለት ቆጣ ብለው ተናገሩ፡፡
ምስክሩም “እንዴ! እኔ እኮ ጥያቄው ለእርስዎ የቀረበ መስሎኛል!“፡፡