የሞት ፍርድ ይቅር?


ከተለያየ ማዕዘን ክርክር ለማቅረብም ስለሚመች የሞት ፍርድ ይቅር የሚል ደጋፍ ቡድን ለማግኘት አስቸጋሪ አይደለም  በአገራችን የዚህ አይነት እንቅስቃሴ ጎልቶ ባይታይም በአንዳንድ የ social network ድረ ገጾች ላይ አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ለማየት ይቻላል በዚህ ረገድ  ፌስ ቡክ “በኢትዮጵያ የሞት ፍርድ ይቅር” የሚል ቡድን ብዙም የነቃ እንቅስቃሴ ባያደርግም ተጠቃሽ ሊሆን ይችላል

የሞት ፍርድ ይቅር የምንል ሰዎች የሚቀጥለውን የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት ውሳኔ ማንበብ ይኖርብናል ከውሳኔው ለመረዳት እንደሚቻለው ተጠሪ ጥፋተኛ ሆኖ ሆኖ የተገኘው በከባድ የግድያ ወንጀል ሲሆን  የአገዳደሉም ሁኔታ ሲታይ ተጠሪው ሟችን አንገቷን በማረድ አይኖቿን በማፍሰስና መላ ሰውነቷን ሰላሣ አምስት ቦታ ላይ በጩቤ በመውጋት የገደላት ከመሆኑም በላይ  ይህንን ወንጀል የፈፀመው የሶስት ዓመት እድሜ ባለው ሕፃን ልጅ ፊት ነው

ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ የወሰነበት ሲሆን ይግባኝ የቀረበለት የጠቅላይ ፍርድ ቤት እጁን በራሱ ጊዜ ለፖሊስ የሰጠ በመሆኑ በሚል ምክንያት በአንድ  የጥፋት ማቅለያ ምክንያት ቅጣቱን ወደ እድሜ ልክ ቀይሮታል በውሳኔው ቅር የተሰኘው የፌደራል ዐቃቤ ህግ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት የሰበር አቤቱታ አቅርቦ የሰበር ችሎቱም የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር ተጠሪው በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል

 

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s