አንድ ጠበቃ በአንዲት ትንሽ የገጠር ከተማ የገጠሩን ውበት እደነቀ ይንሸራሸር ነበር፡፡ ትንሽ መንገድ ከሄደ በኋላ ከመንገዱ ጠርዝ ላይ አደጋ የደረሰ በሚመስል መልኩ ሰዎች ተሰብስበው ግርግር ሲፈጥሩ ይመለከታል፡፡ ወዲያውኑ በዛ ቦታ ላይ የመኪና አደጋ እንደደረሰ የጠበቃ ቀልቡ ከነገረው ነገር ተነስቶ ድምዳሜ ላይ ደረሰ፡፡ በአደጋው ቦታ ዙሪያ ወደተኮለኮሉት ሰዎች በመጠጋት የአደጋውን ዓይነትና ሁኔታ ለማጣራት ቢንጠራራም መግቢያ ቀዳዳ አላገኘም፡፡ በዚህ ጊዜ ፈጣን የጠበቃ ብልጠቱን በመጠቀም ዘዴ ቀየሰና “ወይኔ አባዬ! አሳልፈኝ! ወይኔ አባዬ! አባዬ!” እያለ ሲጮህ ወለል ብሎ ተከፈተለት: እናም በግጭቱ ክፉኛ የተጎዳው አህያ አስፓልቱ ዳር ተዘርሮ ነበር፡፡