የጠበቃ ውሻ የታሰረበትን ገመድ በጥሶ ከቤት በመውጣት በቀጥታ ወደ አቅውራቢያው ስጋ ቤት ካመራ በኋላ ሙዳ ስጋ በጭቆ ያመልጣል፡፡ በውሻው ድርጊት የበገነው የስጋ ቤቱ ባለቤት በቀጥታ ወደ ውሻው ባለቤት ጠበቃ ቢሮ ካመራ በኋላ የሚከተለውን ጥያቄ ይጠይቀዋል፡፡
“የታሰረበትን ገመድ የፈታ ውሻ ከኔ ስጋ ቤት ስጋ ሰርቆ ቢሄድ የውሻውን ባለቤት የስጋዬን ዋጋ ልጠይቀው እችላለሁ?”
ጠበቃውም በእርጋታ ካዳመጠ በኋላ “ያለጥርጥር!” በማለት እርግጠኛ መልስ ይሰጠዋል::
የስጋ ቤቱ ባለቤትም እምቅ ፈገግታ ፊቱ ላይ እየተነበበ በልቡም “ሰራሁልሽ!” እያለ “ዛሬ ጠዋት ያንተ ውሻ ማሰሪውን በጥሶ ግማሽ ኪሎ ስጋ ይዞብኝ ሮጧል፡፡ ስለዚህ 20 ብር ልትከፍለኝ ይገባል፡፡” (የስጋው ዋጋ አዲስ በወጣው የመንግስት የዋጋ ተመን መሰረት ነው!)
ጠበቃውም ያለተቃውሞ ከኪሱ 20 ብር አውጥቶ ይሰጠዋል፡፡ የስጋ ቤቱ ባለቤት በጠበቃው ቅንነት እየተገረመ ሊወጣ ሲል ጠበቃው አስቆመውና አንድ ደረሰኝ ጽፎ “አንተም ለኔ የምትከፍለው 100 ብር አለብህ !” ይለዋል
“የምን መቶ ብር?”
“የህግ ምክር የሰጠሁበት ነዋ”