የአክስዮን ድርሻ መያዣና የቅድሚያ መብት (የሰበር ውሳኔ)


የሰ.መ.ቁ 39255

ሐምሌ 9 ቀን 2001 ዓ.ም

 

 

ዳኞች፡-

ተገኔ ጌታነህ

መንበረፀሐይ ታደሰ

ዓብዱልቃድር መሐመድ

ፀጋዬ አስማማው

አሊ መሐመድ

 

አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነገረ ፈጅ ደረጀ ባዩ ቀረቡ

ተጠሪ፡- 1ኛ. አቶ ተስፋ ዓለሙ ጠበቃ አቶ ወንድአወክ አየለ ቀረቡ

2ኛ. ወ/ሮ ትዕግስት ወንድይፍራው ጠበቃ አቶ አምሣለ ፀሐይ ቀረቡ

 

መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 62715 የካቲት 17 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 38675 ሰኔ 25 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከቱ ነው፡፡

ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በከፍተኛው ፍርድ ቤት አንደኛ ተጠሪ ሁለተኛ ተጠሪ በፍርድ የተወሰነበትን ብር 2,696,482.30 /ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺ አራት መቶ ሰማኒያ ሁለት ብር ከሰላሣ ሣንቲም/ ዕዳው ተከፍሎ እስከሚያልቅ ድረስ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዲከፍል የአፈፃፀም ትዕዛዝ ይሰጥልኝ በማለት የአፈፃፀም ክስ አቅርቧል፡፡ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በአንደኛ ተጠሪና በሁለተኛ ተጠሪ መካከል የቀረበውን ክርክር ከመረመረ በኋላ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ ያላቸው የአክሲዮን ድርሻ ተሽጦ ለአንደኛው ተጠሪ ፍርድ ማስፈፀሚያ እንዲሆን ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ይህንን ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ የተጀመረውን የአፈፃፀም ክስ ከፍርድ ቤት ውጭ ለመጨረስ ተስማምተዋል፡፡ አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ ባደረጉት የአፈፃፀም ስምምነት ሁለተኛ ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ ያለውና ዋጋቸው 1,326,975 /አንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሃያ ስድስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሰባ አምስት ብር/ የሆነ አክሲዮኖች ለአንደኛ ተጠሪ ዕዳ መክፈያነት ወደ አንደኛው ተጠሪ እንዲተላለፉ እና ሁለተኛ ተጠሪ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2006 /2007 ዓ.ም ከአክሲዮን ድርሻው የሚያገኘው ዲቪደንድ ለአንደኛ ተጠሪ እንዲተላለፍ ተዋውለው ለፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የአንደኛና የሁለተኛ ተጠሪን ስምምነት በመቀበል አቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ ባደረጉት የአፈፃፀም ስምምነት መሠረት እንዲፈፅም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በአንደኛና በሁለተኛ ተጠሪ መካከል ያለው የአፈፃፀም ክርክር በዚህ ሂደት ላይ እያለ አመልካች መጋቢት 01 ቀን 2000 ዓ.ም በክርክሩ ጣልቃ ለመግባት እንዲፈቀድለት አመልክቷል፡፡ አመልካች አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ ባደረጉት ስምምነትና ለአንደኛ ተጠሪ ፍርድ ማስፈፀሚያ እንዲሆን ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠበት ሁለተኛ ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ ያላቸው የአክሲዮን ድርሻና እንደ አውሮፖዊያን አቆጣጠር 2006/2007 ዓ.ም ለሁለተኛ ተጠሪ የሚያደርሰው ዲቪደንድ እና ሌሎች ከአክሲዮኖቹ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የሁለተኛው ተጠሪ መብቶች ላይ የቀዳሚነት መብት አለኝ፡፡ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ ያላት የአክሲዮን ድርሻ ሚና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለወሰደው የኦቨር ድራፍት ብድር በመያዣነት ይዣቸዋለሁ፡፡ የሁለተኛው ተጠሪ አክሲዮኖች ሚና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለወሰደው የኦቨር ድራፍት ብድር በመያዣነት የተያዘ መሆኑ በአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ የአክሲዮን መዝገብ ውሰጥ ተመዝግቧል፡፡ የሁለተኛው ተጠሪ የአክሲዮን ድርሻ ማረጋገጫ ሰርተፊኬትም በመያዣነት ተይዞ በእኔ እጅ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ሁለተኛ ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ ያላቸው የአክሲዮን ድርሻና ዲቪደንድ ለአንደኛ ተጠሪ የፍርድ ማስፈፀሚያ እንዲሆንና ወደ አንደኛው ተጠሪ እንዲተላለፍ የሰጠውን የአፈፃፀም ትዕዛዝ ይሰረዝልን በማለት አመልክቷል፡፡

አመልካች ከማመልከቻው ጋር በማያያዝ ይጠቅሙኛል ያላቸውን የፅሑፍ ማስረጃዎች አቅርቧል፡፡ አመልካች ክርክሩን ለማስረዳት

  • ሚና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከአመልካች በኦቨር ድራፍት ብድር ለመውሰድ ላቀረበው ጥያቄ መያዣ ይሆን ዘንድ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ ካሉት የአክሲዮን ድርሻዎች ዋጋቸው ብር 1,250,000 /አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሣ ሺ ብር/ የሆነ አክሲዮኖች እና በሌሎች መዝገቦች ተከራካሪ የሆኑ ስምንት ሰዎች የአክሲዮን ድርሻ በመያዣነት ያቀረበ መሆኑን ገልፆ ያፃፈው ደብዳቤ ከነ አባሪው
  • አመልካች ሚና ትሬዲን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኦቨር ድራፍት ለወሰደው ብር 40,000.000 /አርባ ሚሊዮን ብር/ ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ ካለው የአክሲዮን ድርሻ ውስጥ ዋጋቸው 1,250,000 /አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሣ ሺ ብር/ የሆነ አክሲዮኖችንና የሌሎች ስምንት ሰዎችን የአክሲዮን ድርሻዎች አመልካች በመያዣነት የያዛቸው መሆኑን ገልፆ የአክሲዮን ድርሻዎቹ በመያዣነት አመልካች የያዛቸው መሆኑን በአክሲዮን መዝገብ እንዲመዘገብለት አቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ን በመጠየቅ የፃፈውን ደብዳቤ፣
  • የአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ አመልካች ለሚና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለሰጠው የኦቨር ድራፍት ብድር ዋጋቸው 1,250,000 /አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሣ ሺ ብር/ የሆኑ የሁለተኛው ተጠሪ አክሲዮኖችና በሌሎች መዛግብት ተከራካሪ የሆኑ ስምንት ሰዎች የአክሲዮን ድርሻዎች አመልካች በመያዣነት የያዛቸው መሆኑንና መያዣው በአክሲዮን መመዝገቢያ መዝገብ የተመዘገበና ለሶስተኛ ወገን አክሲዮኖቹ የማይተላለፍ መሆኑን በማረጋገጥ ለአመልካች በአድራሻው የፃፈውና ለሁለተኛ ተጠሪ ግልባጭ የተደረገ ደብዳቤ
  • ሚና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከአመልካች ብር 40,000,000 /አርባ ሚሊዮን ብር/ በኦቨር ድራፍት ብድር የወሰደበት የብድር ውልና ሚና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የወሰደውን ብድር ከነወለዱ ያልከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ
  • በአመልካች ይዞታ ሥር የሚገኘውን የሁለተኛውን ተጠሪ የአክሱዮን ድርሻ ማረጋገጫ ሰርተፊኬትና ሁለተኛው ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ ያለውን የአክሲዮን ድርሻ በመዣነት የያዘ በመሆኑ ሁለተኛው ተጠሪ የሚደርሳቸው ዲቪደንድ ለአመልካች የሚከፈልበትን ሁኔታ እንዲመቻች አመልካች ለአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ በአድራሻው የፃፈውና ለሁለተኛ ተጠሪ ግልባጭ የተደረገ ደብዳቤ
  • የአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች አስረኛ መደበኛ ጉባኤ እንደሚካሄድ በመግለፅ ሁለተኛው ተጠሪ ያሏቸው 50,000 አክሲዮኖች አመልካች በመያዣነት የያዛቸው በመሆኑ ሁለተኛው ተጠሪ አመልካች ካልፈቀደላቸው በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምፅ ለመስጠት የማይችሉ መሆኑ በንግድ ሕግ ቁጥር 329 ንዑስ አንቀፅ 1 እንደተደነገገ ገልፆ ሁለተኛ ተጠሪ በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመገኘትና ድምፅ ለመስጠት ከአመልካች ውክልና ይዘው እንዲቀርቡ ለሁለተኛው ተጠሪ በአድራሻ የፃፈውና ለአመልካች ግልባጭ ያደረገው ደብዳቤ
  • ሁለተኛ ተጠሪ በአቢሲኒያ ባንክ /አ.ማ/ ካለው የአክሲዮን ድርሻ ውስጥ ብር 1,250,000 /አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሣ ሺ ብር/ ዋጋ ያላቸውን አክሲዮኖች ሚና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለወሰዱት ብድር ዋስትና ያስያዘ መሆኑን በመግለፅ አመልካች ከባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤና ሌሎች ስብሰባዎች ለመካፈልና ድምፅ ለመስጠት እንዲችል እንዲፈቅድለት ያፃፈውን ደብዳቤ በማስረጃነት አያይዞ አቅርቧል፡፡

1 Comment

  1. ashenafi says:

    this title directly connects with my job. really i get enough knowledge. thanks a lot

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s