ህግና ፍሬነገር ምንና ምን ናቸው?- የሰበር ስልጣን (የሰበር ውሳኔ)


የሰበር መ/ቁ 43410

ህዳር 30 ቀን 2002 ዓ.ም

 

ዳኞች፡-

1. መንበረፀሐይ ታደሰ

2. ሐጎስ ወልዱ

3. ሂሩት መለሰ

4. ታፈሰ ይርጋ

5. አልማው ወሌ

 

አመልካች፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ – ነ/ፈጅ አሠገደች ጎርፌ

ተጠሪ፡- ሰላም የቴክኒክና የሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል – አልቀረበም

 

ፍ ር ድ

በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ የስነ-ስርዓት ህግን የሚመለከት ነው፡፡ አመልካች የፌ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ ለፌ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የግራ ቀኙ ክርክር በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ አመልካች ባለመቅረቡና ተጠሪ ቀርበው መዝገቡ እንዲዘጋ በመጠየቃቸው ፍ/ቤቱ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(2) መሰረት መዝገቡን ዘግቶታል፡፡ ከዚህ በኋላ አመልካች ለፍ/ቤቱ በታህሣሥ 14 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መዝገቡ እንደገና እንዲከፈትለት የቃል ክርክር በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ ያልቀረበበት ምክንያት በቂ ባለመሆኑ መዝገቡ ሊከፈት አይገባም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል፡፡ የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ትዕዛዞች ላይ ነው፡፡ አመልካች በቅሬታው የቃል ክርክር በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ አመልካች ሳይቀርብ ተጠሪ ከቀረበ መዝገቡ ሊዘጋ የሚገባው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት እንጂ በቁጥር 62(2) አይደለም፣ በቀነ-ቀጠሮው የቀረንበት ምክንያትም የብሔር ብሔረሰቦች በዓል የሚከበርበት ቀን ስለነበር መንገድ በመዘጋጋቱ አርፍደን ስለደረሰን ስለሆነ መዝገቡ እንዲከፈት ይወሰንልን በማለት ጠይቋል፡፡ አቤቱታውም ለሰበር ችሎት ያስቀርባል በመባሉ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በፁሁፍ አቀርበዋል፡፡ መዝገቡም እንደሚከተለው ተመርምሯል፡፡

አመልካች ቃል ክርክር በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ ሳይቀርብ ተጠሪ መቅረቡ አልተካደም፡፡ የባለጉዳዮች ወደ ፍ/ቤት መቅረብና አለመቅረብ የሚያስከትለውን ውጤት ምን እንደሆነ በፍ/ሥ/ሥ/ሕጉ ከቁጥር 65 እና ተከታዮች ባሉት ድነጋጌዎች ተዘርዝረው ተቀምጠዋል፡፡ በዚህ መሰረት ክስ ያቀረበ ሰው ክርክሩ በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ ሳይቀርብ ተከሳሹ ቀርቦ ክሱን በከፊል ወይም በሙሉ ያመነ ከሆነ ላመነው ጉዳይ ፍ/ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት እንደሚችልና ከካደ ደግሞ መዝገቡ እንደሚዘጋ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 ያመለክታል፡፡ በዚህ አንቀፅ ከሳሽና ተከሳሽ የሚለው አነጋገር ይግባኝ ባይ መልስ ሰጪ እንደሚጨምር ከሥነ-ሥርዓቱ ድንጋጌ አንቀጽ 32(2) ሥር መመልከት ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(2) አግባብነት የሚኖረው ክርክር በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ ሁለቱም ተከራካሪዎች ያልቀረቡ ከሆነ ነው፡፡ በተያዘው ጉዳይ ክርክር በሚሰማበት ቀነ-ቀጠሮ ይግባኝ ባይ የነበረው አመልካች ሳይቀርብ ተጠሪ ቀርቧል፡፡ በዚህም ምክንያት አግባብነበት የሚኖረው የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 እንጂ ቁጥር 69(2) አይደለም፡፡ በመሆኑም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 69(2)ን መሰረት አድርጎ መዝገቡን መዝጋቱ ተገቢ አለመሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ነገር ግን ተጠሪ ከስር ፍ/ቤት ጀምሮ ከአመልካች ጋር ሲከራከር የነበረ በመሆኑና ክርክር በሚሰማበት እለት አመልካች ባለመቅረቡ ተጠሪ መዝገቡ እንዲዘጋለት መጠየቁ ተጠቃሎ ሲታይ አቤቱታውን ያላመነ መሆኑን ያመለክታል፡፡ በሌላ በኩል አመልካች በቀነ-ቀጠሮው ያልቀረበው በበቂ ምክንያት ነው ቢልም ፍ/ቤቱ ምክንያቱን መዝኖ በቂ አይደለም የሚለው መደምደሚያ ላይ ደርሷል፡፡ የምክንያቱ በቂ መሆን አለመሆን ደግሞ የማስረጃ ምዘና እንጂ የህግ ክርክር ባለመሆኑ ለሰበር አቤቱታ የሚቀርብበት ነጥብ ነው ሊባል አይችልም፡፡ በአጠቃላይ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መዝገቡን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 73 መሰረት መዝጋት ሲገባው በቁጥር 69(2) መሰረት መዝጋቱ ትክክል ባይሆንም መዝገቡ በመዘጋቱ ግን መሰረታዊ የህግ ስህተት ፈፅሟል ማለት አልተቻለም፡፡

ው ሳ ኔ

  1. የፌ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 39200 ህዳር 30 ቀን 2001 ዓ.ም እና ጥር 18 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጣቸው ትዕዛዞች ፀንተዋል፡፡
  2. ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የቻቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ለመዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ራ/ታ

2 Comments

  1. andualem says:

    I want to broaden my knowledge on the subject matter. It helps me get much info. I find it very nice. Keep it up sharing!

  2. Dave says:

    I want to broaden my knowledge on the subject matter. It helps me get much info. I find it very nice. Keep it up sharing!

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s