- . ቅጥ ያጣ ፍትሐዊነት ቅጥ ያጣ ኢ – ፍትሐዊነት ይሆናል፡፡
ሲስሮ
- . ፍትህ በተግባር የሚታ እውነት ነው፡፡
ቤንጃሚን ዲዜራሊ
- . ማናችንም ብንሆን ሕጉን ካወጡት ሰዎች የበለጠ ህጉን የማክበር ግዴታ የለብንም፡፡
ሶፎክለስ
- . ስልጣናቸው በተደላደለ መሪዎች እይታ እንደ ስህተት በሚቆጠር ጉዳይ ላይ ትክክል ሆኖ መገኘት አደገኛ ነው፡፡
ቮልቴር
- . ሐኪምና ጠበቃ ያው አንድ ናቸው፡፡ ዋናው ልዩነታቸው ጠበቃ ዝም ብሎ ሲዘርፍህ ሐኪም ግን ዘርፎም አይለቅህም፡፡ ይገድልሃል፡፡
አንቷን ቼሆቭ
- . አንዳንዴ ፍትህ ወንጀለኞችን ስትጣቀስ ንጹሐን ላይ ትወድቃለች፡፡
ሳሙኤል በትለር
- . ፍትህን ካልጠበቅናት ፍትህ አትጠብቀንም
ፍራንሲስ ቤከን
- . ጠበቃ ማለት ከጠበቃ እንዲጠብቀን የምንቀጥረው ሰው ነው፡፡
አልበርት ሁባርድ
- . አንተ እንዲኖርህ የምትፈልገው ዓይነት ጠበቃ ባለጋራህም አለው፡፡
ሬይሞንድ ቻንድለር
- . ከሁሉም በላይ ክስና ሙግትን አስወግድ፡፡ ንብረትህን ያባክናል፡፡ ጤናህን ያቃውሳል፡፡ ሕሊናህን ያስታል፡፡
ጂን ደ.ላ.ቡርዬ
- . አለቅጥ ብዙ ህግ ከሚኖር ጨርሶ ባይኖር ይመረጣል፡፡
ሚሼል አ.ደ.ሞንታኝ
- . ጠበቃና ቀለም ቀቢ አፍታም ሳይቆዩ ጥቁሩን ነጭ ማድረግ ይችላሉ፡፡
አባባል