ይግባኝ! ይግባኝ! አሁንም ይግባኝ! (የችሎት ገጠመኝ)


ከሳሽ ሆነው የቀረቡት ሴት በዕድሜ ጠና ያሉ ናቸው፡፡ ታዲያ በችሎት አንዴ መናገር ከጀመሩ የሚያስቆማቸው የለም፡፡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ለእሳቸው እንዲሰጥ ችሎት በቀረቡ ቁጥር መወትወት ስራቸው ነው፡፡ ዳኛው ዕድሜያቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት በጀመሩ ቁጥር በቀስታ ለማረጋጋት ይሞክራሉ፡፡ በመጨረሻ መዝገቡ ለውሳኔ ተቀጥሮ ቀጠሮው ሲደርስ ውሳኔው ተነበበና የእኚህ ከሳሽ ክስ ውድቅ ተደረገ፡፡ ከሳሽ እስከ መጨረሻዋ ዐረፍተ ነገር ድረስ በዝምታ እያዳመጡ ነበር፡፡ ዳኛው “መዝገቡ ስለተዘጋ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ” ብለው መዝገቡን ሲከድኑ በፍጹም ያልተዋጠላቸው ከሳሽ ወደ ዋናው ፍሬ ነገርና አቤቱታ ተመልሰው እጃቸውን እያወራጩ እንደገና እንደ አዲስ ክርክር ጀመሩ፡፡ ውሳኔውን የሰጡት ዳኛ ከሳሽን ለማረጋጋት ቢሞክሩም አልሆነም፡፡ ይሄኔ የዳኛው ትዕግስት አልቆ ኖሮ “ይበቃል እንግዲህ! እማማ! ከዚህ በኋላ በዚህ ፍርድ ቤት የሚቀየር ነገር የለም፡፡ በዚህ ውሳኔ ቅር ከተሰኙ ይግባኝ ማለት ይችላሉ” ሲሉ ቁርጣቸውን ይነግሯቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ከሳሽ ውሳኔው ወዲያውኑ የሚቀየርበት ቀዳዳ የተገኘ መስሏቸው እዛው በቆሙበት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ይግባኝ! ይግባኝ! ይግባኝ ብያለሁ ይግባኝ!” ሲሉ ዳኛው ሳቃቸውን ጨርሰው ስለይግባኝ ስርዓት ካስረዷቸው በኋላ አረጋግተው ሸኝዋቸዋል፡፡

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s