ህግ ነክ ጥቅሶችና አባባሎች


ሰዎች በስቅላት የሚቀጡት ፈረስ ስለሰረቁ አይደለም፡፡ ሰዎች የሚሰቀሉት ፈረሶች እንዳይሰረቁ ነው፡፡

ሎርድ  ሃሊፋክስ

 1. የመንግስት አስተዳደር ጥበብ ታማኝ ሆኖ የመገኘት ጥበብ ነው፡፡

ቶማስ ጆፈርሰን

 1. መከታና ከለላችን በጦር መሳሪያዎቻችን አይደለም፡፡ በሳይንስም አይደለም፡፡ መከታና ከለላችን ህግና ስርዓት ነው፡፡

አልበርት አነስታይን

 1. ዳኛ ዝም ሲል እያሰበ ነው ብለህ ካሰብክ ተሳስተሀል፡፡ ያኔ (ዳኛው) የተዛባ እምነቶቹን ቦታ ቦታ እያስያዘ ነው፡፡

ቴሪ ዎጋን

 1. ለህፃናት ተባብረን የማንቆም ከሆነ ለማንም ተባብረን አንቆምም፡፡

ሜሪያን ራይን አድልመን

 1. ፍትህን ካልጠበቅናት ፍትህ አትጠብቀንም

ፍራንሲስ ቤከን

 1. ጠበቃ ማለት ከጠበቃ እንዲጠብቀን የምንቀጥረው ሰው ነው፡፡

አልበርት ሁባርድ

 1. አንተ እንዲኖርህ የምትፈልገው ዓይነት ጠበቃ ባለጋራህም አለው፡፡

ሬይሞንድ ቻንድለር

 1. አለቅጥ ብዙ ህግ ከሚኖር ጨርሶ ባይኖር ይመረጣል፡፡

ሚሼል አ.ደ.ሞንታኝ

 1. ጠበቃና ቀለም ቀቢ አፍታም ሳይቆዩ ጥቁሩን ነጭ ማድረግ ይችላሉ፡፡

አባባል

 1. ፍርድ ቤት የእምነ በረድ ቤተመንግስት እንደማለት ነው፡፡ በውስጡ ያሉት ሰዎች ጠንካራና ጥርብ ናቸው፡፡

ጂን ደ. ላ ቡርዬ

 1. ማንም ሰው ከህግ በላይ አይደለም፡፡ ከህግ በታችም አይደለም፡፡

ቴዎደር ሩዝቬልት

Latin Maxims

Accipere quid ut justitiam facias non est tam accipere quam extorquere.

ፍትህ ሰጥቶ በምላሹ ሽልማት መቀበል ዞሮ ዞሮ ቅሚያ ነው፡፡ (ፍትህ ሰጥቶ ሽልማት መቀበል ሙስና ነው፡፡)

Accusare nemo debet se, nisi coram Deo.

በእግዜር ፊት ካልሆነ በቀር ማንም ራሱን እንዲከስ (እንዲወነጅል) አይገደድም፡፡

Ad officium justiciariorum spectat unicuique coram eis placitanti justitiam exhubere.

ዳኝነት ለጠየቀ ሁሉ ዳኝነት መስጠት የዳኞች ግዴታ ነው፡፡

Aedifcare in tuo proprrio solo non licet quod alteri noceat.

በራስ መሬት ላይ ሌላውን ሊጎዳ በሚችል ምልኩ ግንባታ ማካሄድ አግባብ አይደለም

Agentes et consentientes pari poena plectentu.

ያደረገውም የተስማማውም እኩል ይቀጣሉ፡፡

Ambulatoria est voluntas defunct us que advitae supermum exitum

ኑዛዜ ተናዛዡ በህይወት ባለበት በማንኛውም ጊዜ ሊቀየር (ሊለወጥ) ይችላል፡፡

Applicatio est vita regulae

የህግ ልቡ ያለው አፈፃፀሙ ላይ ነው፡፡ (የህግ ህይወቱ አፈፃጠሙ)

Arbor dum cresciti lignum dum crescere nescit

እያደገ ከሆነ ዛፍ እንለዋለን፡፡ ካልሆነ እንጨት ነው፡፡

Arma in armatus sumere Jura sinunt

መሳሪያ ባነሳው ላይ መሳሪያ ማንሳትን ህጉ ይፈቅደዋል፡፡

Audi alteram partem

ተቃራኒውን ወገን ስማው፡፡ (አንድ ሰው መከላከያው ሳይሰማለት ሊቀጣ አይገባም)

Bebeficium non datu nisi officii causa

ለተሰራ ስራ ካልሆነ በቀር ደመወዝ አይከፈልም፡፡

Causa caysae est causati

የመንስዔው መንስዔ የውጤቱ መንስዔ ነው፡፡

 

 

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s