ተጠረጠሩበት የወንጀል ክስ ላይ መቃወሚያ አቅርበው፣ በቀረበው የመቃወሚያ መልስ ላይ ብይን ለመስጠት ለትናንትና ተቀጥረው የነበሩት የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበር ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ለይኩንን ጨምሮ አሥር ተከሳሾች በድጋሚ ለብይን ተቀጠሩ፡፡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ስድስተኛ ምድብ ችሎት በትናንትናው ውሎው እንዳስታወቀው፤ ተከሳሾች በቀረበባቸው ክስ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በጽሕፈት ቤት በኩል አቅርበው ብይን መስጠት ነበረበት፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ተጠርጣሪዎች የክስ መቃወሚያ ያቀረቡት ዘግይተው በመሆኑ፣ የቀረበውን መቃወሚያ ደግሞ ፍርድ ቤቱ መመርመርና ማየት አለበት፡፡
የአራተኛ ተጠርጣሪ የወ/ሮ ወንጌላዊት ብርሃኑ ጠበቃ የክስ ቻርጁ የደረሳቸው ትናንት በመሆኑና ክሱን ካዩ በኋላ መቃወሚያ ማቅረብ እንዳለባቸው በመግለጻቸው፤ እንዲሁም ስምንተኛው ተጠርጣሪ አቶ ደረጀ አበበ ችሎት የቀረቡትና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተው የዋስትና መብታቸው (አሥር ሺሕ ብር) የተጠበቀላቸው በትናንትናው ዕለት በመሆኑ፣ የሁሉንም ተጠርጣሪዎች ተቃውሞ መርምሮ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማንብብ
የሚያስቁም የሚያሳቅቁም ነገሮች አሉ በአጠቃለይ ይዘቱም ሆነ ልቀቱን ከልሜዋለው ማኛ ነው የባሰ እንዲከይፈን ይሞከርልን። በቃ ልመርሽ እኔ!