Fiat justitia ruat caelum
ሰማይ ቢገለበጥም እንኳን ፍትህ መሰራት (መሰጠት) አለበት
Frans est celare frqandem
የማጭበርበር ድርጊትን መደበቅ በራሱ ማጭበርበር ነው፡፡
Frusta est potential quae nun quam venit in actum
ያልተገለገሉበት ስልጣን ረብ የለሽ ነው፡፡
Frusta probatur quod probatum non relevant.
ቢረጋገጥ ለጉዳዩ አግባብነት የሌለውን ነገር ማረጋገጥ ፋይዳ የለውም
Haeres haeredis mei est mens haeres
የወራሼ ወራሽ ወራሼ (የኔም ወራሽ) ነው፡፡
Hora non est multum de substanti negotii, licet in appello de ea aliquando
ጦርነት ያወጁብን ወይም ያወጅንባቸው ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ የተቀሩት በሙሉ ሴረኞች ወንበዴዎች ናቸው፡፡
Idem agens te patients esse non potest
ተወካይ በተመሳሳይ ጊዜ አድራጊም ተደራጊም (ነገሩ የሚደረግለት) ሰው መሆን አይችልም፡፡
Idem est facere et nolle prohibere cum posis
አንድን ድርጊት መፈጸምና ማስቆም የምትችለው ድርጊት መተው ሁለቱም አንድ ናቸው፡፡
Isem non esse et non apparere
ህልውና ማጣትም መጥፋትም ሁለቱም አንድ ናቸው፡፡
Id tantum possumus quad de jure possumus.
ማድረግ የምንችለው በህጋዊ መንገድ ማድረግ የምንችለውን ብቻ ነውው፡
Ignorantia juris non excusat
ህግን አለማወቅ ይቅርታ አያሰጥም
In conventionibus, contrahertium voluntas potius quam verba spectaribplacuit
በውል ውስጥ ከተዋዋይ ወገኖች ቃል ይልቅ ሃሳባቸው መታየት አለበት
Inde datae leges ne fortiori omnia posset
ህግ የቆመው ኃይለኛው ወገን ያልተገደበ ስልጣን እንዳይኖረው ነው፡፡
Judex bonus nihil ex arbitrio suo faciat nec propositone docmesticae voluntaris, sed juxta leges et jura pronuncite.
ጥሩ ዳኛ ከራሱ የግል ፍላጎትና ምርጫ ተነሳስቶ ምንም ነገር ማድረግ የለበትም፡፡ ይልቅስ በህግና በፍትህ እተመራ ዳኝነት ሊሰጥ ይገባዋል፡፡
Judex non reddit plus quam quod petens ipse requirit.
ዳኛ ከሳሹ ራሱ ከጠየቀው በላይ ዳኝነት ሊሰጥ አይገባም