የግብፅ ኩባንያ በቤኒሻንጉል ከፍተኛ የወርቅ ክምችት አገኘ


የግብፅ ኩባንያ በቤኒሻንጉል ከፍተኛ የወርቅ ክምችት አገኘ.

የግብፁ የማዕድን ኩባንያ አስኮም የሚሌኒየም ግድብ በሚገነባበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ባካሄደው የወርቅ ፍለጋ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ማግኘቱ ተረጋገጠ፡፡ የግብፁ ኩባንያ አስኮም ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ በክልሉ 8,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ ወርቅና የከበሩ ማዕድናትን ሲፈልግ ቆይቷል፡፡

ቦታውን ከማዕድን ሚኒስቴር የተረከበው ኩባንያው፣ የማዕድን ፍለጋውን ኢትዮጵያን ጨምሮ በሱዳንና አልጀሪያ በተለይም ‹‹በዓረብ ኑብያን ሺልድ›› ክልል ውስጥ አጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል፡፡

ከኩባንያው የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በዓረብ ኑቢያን ሺልድ ክልል ውስጥ በተለይም በምዕራብ ኢትዮጵያ ቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ ወርቅና ከወርቅ ጋር ተቀራራቢነት ያላቸውን የማዕድናት ክምችት አግኝቷል፡፡

የማዕድን ሚኒስቴር የማዕድን ሥራዎች ቁጥጥር መመሪያ ኃላፊ አቶ ገብረ እግዚአብሔር መኮንን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የኩባንያው ግኝት ለአገሪቱ ትልቅ ትርጉም አለው፡፡

የማዕድን ፍለጋ አስቸጋሪ እንደመሆኑ መጠን ኩባንያው በትዕግስት እዚህ ውጤት ላይ መብቃቱ አስደሳች መሆኑን አቶ ገብረ እግዚአብሔር ገልጸው፣ ኢኮኖማያዊ ጠቀሜታውም የጎላ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

አስኮም በግብፅ የካፒታል ገበያ እ.ኤ.አ. በ2009 የተቋቋመ ኩባንያ ነው፡፡ በማዕድን ፍለጋና ማውጣት ሥራ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን አትራፊም ነው፡፡

የወርቅ ማዕድን በዚህ ክልል ያገኘው አስኮም ብቻ አይደለም በሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ የተመሠረተው ማድሮክ ጐልድም የወርቅ ክምችት አግኝቷል፡፡ ሚድሮክ ጐልድ ከማዕድን ሚኒስቴር በቤንሻንጉል ክልል ቡለን ወረዳ ሞር አካባቢ ከሁለት ዓመት በፊት የወርቅ አሰሳ ፈቃድ አግኝቷል፡፡

ሙሉ ዜናውን ለማንበብ

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s