– የሊዝ ቦርድ ይፈርሳል
– ከጨረታ ውጭ ቦታ የሚሰጥ ኃላፊ በገንዘብና በእስራት ይቀጣል
በርካታ ግድፈቶችና ክፍተቶች ነበሩበት የተባለውንና እስካሁን ሲሠራበት የቆየውን የሊዝ አዋጅ ይተካል የተባለው ረቂቅ አዋጅ የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
የከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ፖሊሲን ለማስፈጸም የክልልና የከተማ አስተዳደሮች ጥብቅ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡
የከተማ ልማትና የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴርና ጉዳዩ በቀጥታ ይመለከታቸዋል በተባሉ አካላት የተዘጋጀው አዲሱ ረቂቅ የሊዝ አዋጅ ቀደም ብሎ ከነበረው አዋጅ ጋር ሲነጻጸር ሰፊ ልዩነት ያለው መሆኑም ታውቋል፡፡