የአዋሽ ባንክ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የመጨረሻ የመፋረጃ ሐሳብ አቀረቡ


የአዋሽ ባንክ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የመጨረሻ የመፋረጃ ሐሳብ አቀረቡ.

ሪፖረተር

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ መጋቢት 7 ቀን 2003 ዓ.ም. በመሠረተባቸው ክስ ሲከራከሩ የነበሩት የቀድሞው የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ለይኩን ብርሃኑን ጨምሮ ስምንት ተጠርጣሪ ተከሳሾች፣ “በነፃ መሰናበት አለብን” በማለት የመጨረሻ የመፋረጃ ሐሳባቸውን ሐምሌ 13 ቀን 2003 ዓ.ም. አቀረቡ፡፡ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ስድስተኛ ወንጀል ችሎት የመጨረሻ የመፋረጃ ሐሳባቸውን ያቀረቡት ስምንት ተጠርጣሪዎች ሲሆኑ፣ አቶ ለይኩን ባቀረቡት ባለ ስድስት ገጽ የመፋረጃ ሐሳብ፣ የቀረበባቸውን ክስ ዓቃቤ ሕግ በምስክሮቹም ሆነ በሰነድ ማስረጃዎቹ እንዳላስረዳቸው ገልጸዋል፡፡ እሳቸውም በመከላከያ ምሰክሮቻቸው ባቀረቡት ሰነድ በሚገባ ያስረዱና የተከላከሉ መሆናቸውን በመግለጽ በነፃ እንዲያሰናብታቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡

አቶ ለይኩን የባንኩ ፕሬዚዳንት ሆነው ሲሠሩ በተጭበረበሩ ሰነዶች ከባንኩ በድምሩ 6,196,760.88 የአሜሪካ ዶላር ሕገወጥ በሆነ መንገድ እንዲፈቀድ አድርገዋል የተባሉትን፣ ባቀረቡዋቸው ዝርዝር ማስረጃዎች ማስረዳታቸውንና ዓቃቤ ሕግም ያቀረበባቸውና ያረጋገጠበት ሰነድ አለመኖሩን በመፋረጃ ሐሳባቸው አስታውቀዋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በአቶ ለይኩን ላይ ያቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና ከራሱ ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ የተገኙ ስለ መሆናቸው አቶ ለይኩን ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዱ፣ ዓቃቤ ሕግ ከብሔራዊ ባንክ ያቀረባቸው ሰነዶች የባንኩ የውጭ ምንዛሪ ዕለታዊ ይዞታን በተመለከተ ያወጣውን መመርያና ከባንኩ የተወሰዱ የምርመራ ሪፖርቶች ናቸው፡፡ ከአዋሽ ባንክ የተወሰዱት ማስረጃዎች ደግሞ ባንኩ በውጭ ምንዛሪ አፈቃቀድ ዙርያ በባንኩ ቁጥጥር መምርያ እ.ኤ.አ. በየካቲት 2010 በፕሬዚዳንቱ በተሰጠ ትዕዛዝ መሠረት ለዲሲፕሊን ኮሚቴ የቀረቡ ሪፖርት፣ የውሳኔ ሐሳቦች፣ በባንኩ ስለነበረው ትርፍ የውጭ ምንዛሪ መጠን የባንኩ የውጭ ኦዲተሮች (ኤኤ ብሮምሄድና ኩባንያ) ለባንኩ ያቀረቡት ሪፖርቶችና በውጭ ምንዛሪ አፈቃቀድ ዙርያ በተሠራው ጥፋት የፕሬዚዳንቱ ሚና እንዲመረመር በባንኩ ቦርድ የተቋቋመው አምስት አባላት የሚገኙበት አጣሪ ኮሚቴ የቀረበ ሪፖርት ነው፡፡

ሙሉ ዜናውን ለምንበብ

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s