ስለ ግል ድርጅት ሰራተኞች ጡረታ ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 715/2ሺ3


አዋጅ ቁጥር 715/2ሺ3

ስለ ግል ድርጅት ሰራተኞች ጡረታ ለመደንገግ የወጣ አዋጅ

የማህበራዊ ዋስትናን ስርዓት በማስፋፋት ደረጃ በደረጃ ለዜጎች እንዲዳረስ ማድረግ ከአገሪቷ ማህበራዊ ፖሊሲ አንዱ አካል በመሆኑ፤

የስርዓቱ መስፋፋትና ተጠናክሮ መቀጠል ለማህ በራዊ ፍትሕ፣ ለኢንዱስትሪ ሰላም፣ ለድህነት ቅነሳና ለልማት ጉልህ አስተዋፆ ስለሚኖረው፤

የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ ዐቅድ እንዲኖ ራቸው ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 5(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

ይህ አዋጅ ‹‹የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2ሺ3›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡-

“‹የግል ድርጅት ሠራተኛ” ማለት ማንኛዉም በግል ድርጅት በቋሚነት በመቀጠር ደመወዝ እየተከፈለው የሚሠራ ሰው ነው፤

2/“ቋሚ ሰራተኛ” ማለት በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ላልተ ወሰነ ጊዜ ለተቀጠረ ሠራተኛ የተሰጠውን ትርጓሜ ይይዛል፤

3/ “የግል ድርጅት” ማለት ለንግድ፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለእርሻ፣ ለኮንስትራክሽን፣ ለማህበራዊ አገል ግሎት ወይም ለሌላ ሕጋዊ ዓላማ የተቋቋመ ሠራተኛ ቀጥሮ ደመወዝ እየከፈለ የሚያሠራ የግል ተቋም ወይም ሰው ሲሆን የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን ይጨም ራል፤

4/‹‹መንግሥት›› ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራ ላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል መንግሥትን እና የክልል መንግሥታትን ያጠቃልላል፤

5/‹‹ክልል›› ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ #7(1) የተመለከተው ማንኛውም ክልል ሲሆን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተሞች አስተዳደሮችን ይጨምራል፤

6/‹‹የግል ድርጅት አገልግሎት›› ማለት በግል ድርጅት ሠራተኞች የሚፈጸም አገልግሎት ነው፤

7/‹‹አበል›› ማለት የአገልግሎት ጡረታ አበል፣ የጤና ጉድለት ጡረታ አበል፣ የጉዳት ጡረታ አበል ወይም የተተኪዎች ጡረታ አበል ሲሆን የዳረጎት አበልና የጡረታ መዋጮ ተመላሽን ይጨምራል፤

8/‹‹ደመወዝ›› ማለት ለሥራ ግብርና ለማንኛ ውም ሌላ ጉዳይ ተቀናሽ የሚሆነው ሂሣብ ሳይነሣለት አንድ የግል ድርጅት ሠራተኛ በመደበኛ የሥራ ሰዓት ለሚሰጠው አገል ግሎት የሚከፈለው ሙሉ የወር ደመወዝ ነው፤

9/‹‹ባለመብት›› ማለት በዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች መሠረት አበል የሚያገኝ ወይም አበል ለማግ ኘት የሚያስፈልጉትን ሁኔታዎች የሚያሟላ የግል ድርጅት ሠራተኛ ወይም ተተኪ ነው፤

10/‹‹ተተኪ›› ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ “9 ንዑስ አንቀፅ (3) የተዘረዘሩትን ያጠቃል ላል፤
11/‹‹የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ዐቅድ›› ማለት በዚህ አዋጅ ለሚሸፈኑ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ አበል ክፍያና አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ስርዓት ነው፤
12/‹‹የጡረታ ፈንድ›› ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት ለሚሰበሰብ የጡረታ መዋጮና ለሚፈጸም የአበል ክፍያ ተግባር የተቋቋመ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ ፈንድ ነው፤
13/‹‹ኤጀንሲ›› ማለት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 202/2ሺ3 የተቋቋመው የግል ድር ጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ነው፤
14/‹‹ሰው›› ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤
15/በወንድ ፆታ የተገለጸው የሴትንም ያካት ታል::

3  የተፈጻሚነት ወሰን

1  የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን የጡረታ ጥቅም የሚመለከተው የአዋጅ ቁጥር 270/1994 ድንጋጌ እና አገሪቷ ተዋዋይ ወገን የሆነችባቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንደተጠበቁ ሆኖ ይህ አዋጅ በዜግነት ኢትዮጵያዊ ለሆኑ የግል ድርጅ ቶች ሠራተኞች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፤
2/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም፡-
ሀ) ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት በተቋ ቋሙ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ ዐቅድ ወይም ፕሮቪደንት ፈንድ ሽፋን ያላቸው ሠራተኞች በነ በራቸው ዐቅድ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚነታቸውን ለመቀ ጠል ሊወስኑ ወይም በዚህ አዋጅ ስለሚሸፈኑበት ሁኔታ ሊስማሙ ይችላሉ፤
ለ)የሃይማኖት ድርጅቶች እና የፖለ ቲካ ድርጅቶች ሠራተኞች እና መደ በኛ ባልሆነው የሥራ ዘርፍ የተሰ ማሩ ሰዎች በፈቃደኝነት ላይ ተመ ሥርቶ በዚህ አዋጅ መሠረት የጡ ረታ ሽፋን እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

3/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም፡-
ሀ)  የቤት  ሠራተኞች፤ እና
ለ)መንግሥታዊ የዓለም አቀፍ ድር ጅቶችና የውጭ መንግሥታት ዲፕ ሎማቲክ ሚሲዮኖች  ሠራተኞች፤
በዚህ አዋጅ አይሸፈኑም፡፡

አዋጁን ሙሉውን ለማንበብ

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s