የታላቁ ቤተ መንግሥት ግምጃ ቤት ኃላፊ በ12 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተጠየቀ


የታላቁ ቤተ መንግሥት ግምጃ ቤት ኃላፊ በ12 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተጠየቀ.

ሪፖርተ

በአራዳ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 15/16 ክልል ልዩ ቦታው አራት ኪሎ ታላቁ ቤተ መንግሥት ውስጥ አንድ የግምጃ ቤት ኃላፊና አንድ ሾፌር በ12 እና በአምስት ዓመታት ፅኑ እስራት፣ በ20 ሺሕ ብርና በአምስት ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ዓቃቤ ሕግ ጠየቀ፡፡ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በትናንትናው ዕለት ቅጣቱን የጠየቀባቸው ከዓመት በፊት ክስ መስርቶባቸው በነበሩትና የግምጃ ቤት ኃላፊ በሆኑ ቄስ ታደሰ ኃይሌና ሾፌር በነበሩት አቶ ሙላቴ መሸሻ ላይ ነው፡፡ የቀረበባቸውን ከባድ የእምነት ማጉደልና ሙስና ክስ መከላከል ባለመቻላቸው የቅጣት ማክበጃ ሐሳብ ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡

የታላቁ ቤተ መንግሥት ግምጃ ቤት ኃላፊ የነበሩት ቄስ ታደሰ፣ ከ1978 እስከ 2001 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ኃላፊ ሆነው ሲሠሩ፣ ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለማግኘት አስበው በአደራ ከተረከቡትና በቅርስነት ከተመዘገቡት የመንግሥት ንብረቶች ውስጥ 19 ዓይነት ቅርሶችን ማጉደላቸውን የዓቃቤ ሕግ የክስ ቻርጅ ይገልጻል፡፡

ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት መስከረም 11 ቀን 2002 ዓ.ም. ባቀረበው የክስ ማመልከቻ እንደገለጸው፣ ኃላፊው ሰባት የተለያየ ይዘት ያላቸው የዝሆን ጥርሶች፣ የአንበሳ ምስል ያላቸው ስምንት ኩባያዎች፣ አንድ ፋኖስ፣ 4009 ባለዘውድ ዓርማ የልብስ ቁልፎች፣ ሁለት የኮት ቁልፎች፣ አንድ የሴት አንበሳ ቆዳ አጉድለዋል፡፡ በተጨማሪ 23 ከቀንድ የተሠሩ መለኪያዎች፣ 164 ቀ.ኃ.ሥ የሚሉ ባለ ዓርማ ብርሌዎች፣ አራት ከብርጭቆ የተሠሩ ማብረጃዎች፣ ሁለት ከቀንድ የተሠሩ ዋንጫዎች፣ ሰባት ከያሻል ጨው የተሠሩ ቅርሶች፣ ሁለት የመርፌ ቅርጽ ያላቸው ድቡልቡል የሆኑ ብርጭቆ ማጉሊያዎች፣ አንድ ካፖርት፣ ስድስት የእሳት መዛቂያ አካፋዎች፣ ሦስት የእሳት መቆንጠጫዎች፣ ሦስት የእሳት ወናፍ (ማራገቢያ)፣ ሁለት የአመድ መጥረጊያ ብሩሽ፣ አምስት የእሳት መቆስቆሻና ሁለት የአንበሳ ቅርፅ ያለው የሳሎን እሳት መከለያ አጉድለዋል፡

ሙሉ ዜናውን ለማንበብ

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s