ለዳኛው ሹክ በያቸው! (የችሎት ቀልዶችና ሌሎችም!)


በስም ማጥፋት ወንጀል ጉዳይ ዐቃቤ ህግ  ምስክሯን ዋና ጥያቄ አየጠየቀ ነው

ዐቃቤ ህግ  ” ተከሳሽ ተበዳይን ምንድነው ያለቻት? አንዱንም ሳትደብቂ ቃል በቃል  በትክክል ከተከሳሽ አፍ የወጣውን ቃል ንገሪን!? በዚህን ጊዜ ምስክሯ አንዴ የተከበሩትን ዳኛ ሌላ ጊዜ ሰፍ ብሎ ከአፏ የሚወጣውን ቃል የሚጠባበቀውን ዐቃቤ ህግ  እያየች ስትቅለሰለስ “ንገሪን እንጂ!” በማለት አፋጠጣት

ምስክሯ ግን አሁንም በመቅለስለስ ” ኧረ ጌታዬ! ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ቃል ነው እንኳን እዚህ የተከበረው ፍርድ ቤት ቀርቶ መሸታ ቤት ውስጥ እንኳን የሚነገር አይደለም”

በዚህን ጊዜ ዐቃቤ ህግ ፈገግ እንደማለት እያለ “እ!…እንደዛ ከሆነ ለዳኛው ሹክ በያቸው!”

አንጀባ (የችሎት ገጠመኝ)

በሐረሪ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አንዲት የፍርድ ባለመብት የአፈፃፀም መዝገብ ከፍታ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት እንደ ፍርዱ ተፈጽሞላት በቀጠሮው ቀን ቀረበች፡፡ ዳኛው እሺ “እንደ ፍርዱ ተፈፅሞልሻል?” ሲሉ የፍርድ ባለመብትን ጠየቁ፡፡ የፍርድ ባለመብትም ትንሽ ቅር እያላት “አዎ! ግን?” ብላ መናገር ስትጀምር ዳኛው አቋረጧትና “ግን ምን?” በማለት መልሰው ጠየቋት፡፡ እሷም “እንደፍርዱ ተፈጽሞልኛል ግን የፍርድ ባለ ዕዳ አሁንም አንጀባውን አላቋረጠም!” ስትል አቤቱታዋን አሰምታለች፡፡ ሆኖም በውሳኔው ላይ አንጀባን አስመልክቶ የተሰጠ ውሳኔ ስለሌለ ፍርድ ቤቱ የፍርድ ባለመብትን እንዲሁ ሸኝቷታል

ልዩ  ልዩ

ከግራ ወደቀኝ እየተመላለሰ ባለማቋረጥ ለረጅም ጊዜ ክርክሩን በማቅረብ ላይ ያለ አንድ ሞቅ ያለው ጠበቃ በወሬው መሐል ቆም ብሎ “እየተከተሉኝ ነው ጌታዬ?” ሲል ዳኛውን ይጠይቃቸዋል፡፡ ዳኛውም “አዎ በቅርበት እተከተልኩህ ነው፡፡ ግን ግራ የገባኝ ነገር ወዴት ነው የምትሄደው?” በማለት መልሰው በነገር ጠቅ አድርገውታል፡፡

ሕግ ነክ ጥቅሶች

ዳኛ ሽጉጥ መታጠቅ ሲጀምር ፍርድ ቤቶች መዘጋት አለባቸው፡፡

ስቴፈን ጀጆንሰን ፊልድ – ዳኛ (መሳሪያ እንዲታቅ ሲጠየቅ የሰጠው መልስ)

ማኅበራዊ ዋስትና ይቅር የሚባል ከሆነ ከሀብታም መጀመር አለበት፡፡

ማክ ሞርጋን

ጥሩ ጠበቃ የምለው በሙያው የተካነና ጉዳዩን ከተለያየ ማዕዘን ለማየት የሚችለውን ሳይሆን ውስጥህን አንብቦ በአንተ ጉዳይ ከልቡ ገብቶበት ከማጥ ውስጥ ሳይቀር ሊያወጣህ የሚችለውን ነው፡፡

ራልፍ ዋልደ ኤመርሰን

ስልጣናቸው በተደላደለ መሪዎች እይታ እንደ ስህተት በሚቆጠር ጉዳይ ላይ ትክክል ሆኖ መገኘት አደገኛ ነው፡፡

ቮልቴር

ሐኪምና ጠበቃ ያው አንድ ናቸው፡፡ ዋናው ልዩነታቸው ጠበቃ ዝም ብሎ ሲዘርፍህ ሐኪም ግን ዘርፎም አይለቅህም፡፡ ይገድልሃል

አንቷን ቼሆቭ

ጠበቃና ቀለም ቀቢ አፍታም ሳይቆዩ ጥቁሩን ነጭ ማድረግ ይችላሉ፡፡

አባባል

ማንም ሰው ከህግ በላይ አይደለም፡፡ ከህግ በታችም አይደለም፡፡

ቴዎደር ሩዝቬልት

የመንግስት አስተዳደር ጥበብ ታማኝ ሆኖ የመገኘት ጥበብ ነው፡፡

ቶማስ ጀፈርሰን

ወርቃማ የላቲን አባባሎች

Accipere quid ut justitiam facias non est tam accipere quam extorquere.

ፍትህ ሰጥቶ በምላሹ ሽልማት መቀበል ዞሮ ዞሮ ቅሚያ ነው፡፡ (ፍትህ ሰጥቶ ሽልማት መቀበል ሙስና ነው፡፡)

Accusare nemo debet se, nisi coram Deo.

በእግዜር ፊት ካልሆነ በቀር ማንም ራሱን እንዲከስ (እንዲወነጅል) አይገደድም፡፡

Ad officium justiciariorum spectat unicuique coram eis placitanti justitiam exhubere.

ዳኝነት ለጠየቀ ሁሉ ዳኝነት መስጠት የዳኞች ግዴታ ነው፡፡

ለተሰራ ስራ ካልሆነ በቀር ደመወዝ አይከፈልም፡፡

Causa caysae est causati

የመንስዔው መንስዔ የውጤቱ መንስዔ ነው፡፡

Consenensus, non conclubitus, facit matrimonium

(የተጋቢዎች) ፍቃድ እንጂ አንሶላ መጋፈፍ ጋብቻን አይመሰርትም፡፡

Id tantum possumus quad de jure possumus.

ማድረግ የምንችለው በህጋዊ መንገድ ማድረግ የምንችለውን ብቻ ነው፡

Judicis officium est opus diei suo perficere

የዕለቱን ስራ በዕለቱ መጨረስ የዳኞች ግዴታ ነው

Minus solvit qui tardius solvit

አዘግይቶ የሚከፍል አሳንሶ ይከፍላል

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s