የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሕብረት ስለሚመሰርቱበት ሁኔታ የወጣ መመሪያ ቁጥር 1/2002DOWNLOAD የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሕብረት ስለሚመሰርቱበት ሁኔታ የወጣ መመሪያ ቁጥር 1/2002

1.    አውጪው ባለሥልጣን

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001 አንቀጽ 15 (3) እና አንቀጽ 55 (2) እንዲሁም በደንብ ቁጥር 168/2001 አንቀጽ 34 መሰረት የሚከተለውን መመሪያ አውጥቷል፡፡

2. አጭር ርዕስ ይህ መመሪያ “የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ህብረት መመሪያ ቁጥር 1/2002” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

3. ትርጓሜ በዚህ መመሪያ ውስጥ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጓሜ የሚያሠጥ ካልሆነ በስተቀር፤

1. “አዋጅ” ማለት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣ አዋጅ ቁጥር 621/2001 ነው፡፡

2. “ደንብ” ማለት የበጎ አድራጐት ድርጅቶች እና ማህበራት ምዝገባ እና አስተዳደር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 168/2001 ነው፡፡

3. “ኤጀንሲ” ማለት በአዋጁ አንቀጽ 4 መሰረት የተቋቋመው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ነው፡፡

4. “ጠቅላላ ጉባኤ” ማለት የህብረቱ መስራች አባላትና በህብረቱ

መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ተቀባይነት ያገኙ ሌሎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ወይም ማህበራትን በአባልነት ያቀፈ የህብረቱ የበላይ አካል ነው፡፡

5. “የሥራ አመራር ቦርድ ማለት በህብረቱ ጠቅላላ ጉባዔ የሚመረጥና የህብረቱን እንቅስቃሴ በቅርበት የሚከታተል አካል ማለት ነው፡፡

6. በአዋጁ አንቀጽ 2 እና በደንቡ አንቀጽ 34 የተሠጡ ትርጓሜዎች ለዚህ መመሪያም ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

7. “ህብረት” ማለት በኤጀንሲው ወይም ስልጣን ካለው የክልል መንግስት መዝጋቢ አካል ህጋዊ ሰውነት ያላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ማህበራት የጋራ ሥራቸውንና አላማቸውን እንዲያስተባብር፤ እንዲሁም በዚህ መመሪያ አንቀጽ 5(2) ሥር የተዘረዘሩ ተግባራትን ለማከናወን በበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ ወይም ማህበራቱ የበላይ አካል ውሳኔ የሚቋቋም ራሱን የቻለ ተቋም ነው፡፡

DOWNLOAD የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሕብረት ስለሚመሰርቱበት ሁኔታ የወጣ መመሪያ ቁጥር 1/2002

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s