የኅብረተሰቡን የልማት ችግር በመቅረፍ ላይ የተሰማራ አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት የከተማው ነዋሪ ሁሉ የቻለውን ያህል ሲረዳ አንድ እጅግ የተሳካለት ሀብታም ጠበቃ ግን ምንም መዋጮ እንዳልሰጠ ሲረዳ የገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሊቀመንበሩን ለገንዘብ ጥያቄ ወደ ጠበቃው ይልካል፡፡ ሊቀመንበሩ ወደ ጠበቃው ቢሮ ሲገባ የትህትና ሰላምታ ካቀረበ በኋላ ቁጭ ብሎ የመጣበትን ጉዳይ ማስረዳት ጀመረ፡፡
“ምንም እንኳን የእርስዎ ዓመታዊ ገቢ ከሚሊዮን ብር በላይ ቢሆንም ባደረግነው ጥናት መሠረት ለድርጅታችን ሰባራ ሳንቲም እንኳን እርዳታ አልሰጡም፡፡ ሳይማር ላስተማሮት ህብረተሰብ ችግሩን ለመቅረፍ የተቻለዎትን መለገስ አይፈልጉም?” በማለት ጥያቄ አቀረበ፡፡
ጠበቃውም ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆም ብሎ አሰበና “ስለ እኔ ገቢ እና መዋጮ አለመስጠት ጥናት ስታደርጉ እግረመንገዳችሁን አሮጊት እናቴ ለረጅም ጊዜ የአልጋ ቁራኛ ሆና እንደምትሰቃይና ከአቅሟ በላይ የሆነ የህክምና ወጪ እንደሚጠብቃትስ ጥናት አድርጋችኋል?” ሲል ሊቀመንበሩን አፋጠጠው፡፡ በነገሩ ሃፍረት የተሰማው ሊቀመንበር “በእውነት እኔ በበኩሌ አልሰማሁም!” በማለት እየተቅለሰለሰ ምላሽ ሰጠ፡፡ ጠበቃው ብሶቱን ቀጠለ “እንደገናስ በጦርነት ቆስሎ የመጣው ወንድሜ ዓይኖቹ ታውረው ከተሸከርካሪ ወንበር መነሳት አቅቶት ሚስቱንና ስድስት ልጆቹን ማስተዳደር እንዳቃተውስ በጥናታችሁ አካታችኋል?”
በዚህን ጊዜ ልቡ የተነካው ሊቀመንበር ባቀረበው የልመና ጥያቄ ተፀፅቶ ይቅርታ መጠየቅ ሲጀምር ወዲያውኑ ጠበቃው አቋረጠውና “የእህቴ ባል በአሰቃቂ የመኪና አደጋ ሲሞት ጥሎአቸው የሄደው ሶስት ጨቅላ ህፃናት የሚላስ የሚቀመስ የላቸውም፡፡ ቤታቸውም በባንክ ዕዳ ተይዟል፡፡ ይህንንስ ጥናት አድርጋችኋል?” ጠበቃው ድምጹ እየናረ ምሬቱን ገለጸ፡፡ ሊቀመንበሩ እፍረቱ የባሰ እየጨመረ “ውይ አኔ እኮ ይህንን ሁሉ አላውቅም” ካለ በኋላ ብድግ ብሎ በቀስታ ወደ መጣበት ሊመለስ ሲል ጠበቃው አስቆመውና
“እና ለነዚህ ሁሉ ሰባራ ሳንቲም ካልሰጠሁ ለምን ብዬ ነው ለናንተ የምሰጠው?”

it is so amazing .i like this web tank you