ጠጥቶ ፈረስ መንዳት

ጠጥቶ መንዳት ክልክል ነው፡፡ ይህን ህግ ጠጥተው የማውቁ ሆነ ነድተው የማውቁ ሁሉ ያውቁታል፡፡ ግን ምን መንዳት ነው የተከለከለው? ለምሳሌ የሚነዳው መኪና መሆኑ ቀርቶ ፈረስ ቢሆንስ? በአሜሪካ ፔንስላቫኒያ ግዛት ፍርድ ቤት በቀረበ ጉዳይ ላይ ይኸው ነጥብ ሁሉንም ዳኞች ባያስማማም ፈረስም፤ መኪናም ያው ነው የሚል አቋም ተይዞ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡ (Pennsylvania v. Noel, 857 A.2d 1283 (Pa. 2004)… Read More ጠጥቶ ፈረስ መንዳት

ቸልተኝነት እና አስተዋዩ ውሻ

 ከውል ውጩ በሚደርስ ኃላፊነት ህግ ውስጥ የቸልተኝነት ጥያቄ ከተነሳ ምላሹ ለብዙ ፍርድ ቤቶች ብዙውን ጊዜ አስቸጋሪ ነው፡፡ በብዙ የህግ ስርዐቶች ውስጥ ተቀባይነት ያገኘው የቸልተኝነት መለኪያ “የአንድ አስተዋይ ሰው ሚዛን” ሲሆን ይህም አንድ አስተዋይ ሰው በተመሳሳይ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆን ኖሮ ምን እንደሚያደርግ በመላምታዊ ፍሬ ነገር ላይ ተመስርቶ ማሰላሰልና ድምዳሜ ላይ መድረስን ይጠይቃል፡፡ እንግዲህ ቸልተኝነትን በአንድ አስተዋይ… Read More ቸልተኝነት እና አስተዋዩ ውሻ

አስገራሚ ክሶች

አሜሪካ ውስጥ ማንም ሰው በማንም ሰው ላይ በማንኛውም ጉዳይ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ክስ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ የፌዝ የሚመስሉ ክሶች ፍርድ ቤት ፋይል ተከፍቶላቸው የሚቀርቡት በስራ ፈቶች ብቻ ሳይሆን ያወቁና የነቁ በሚባሉ ሰዎች ጭምር ነው፡፡ የፌዝ ክሶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመብዛታቸው የተነሳ ይህንኑ ለመከላከል (Citizens against lawsuit abuse) የሚባል ድርጅት ተቋቁሟል፡፡ ከነዚህ የፌዝ የሚመስሉ ክሶች በምሳሌነት የሚከተሉት… Read More አስገራሚ ክሶች

የጉዳት ካሳ ለዛፍ? (ፍርድ በግጥም)

በፊሸር እና ሎው (Fisher Vs. Lowe) መዝገብ ከሳሽ በአሜሪካ ሚቺጋን የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበው ክስ ተከሳሹ መኪናውን እየነዳ የከሳሽን የዋርካ ዛፍ ገጭቶ ጉዳት ስላደረሰ ካሳ እንዲከፈለው የሚጠይቅ አቤቱታ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ታዲያ ክሱን ውድቅ ያደርግና ተከሳሽን በነፃ ያሰናብተዋል፡፡ በጣም በሚወደው ዛፍ ላይ የደረሰው ጉዳት ያንገበገበው ከሳሽ ግን ፍትህ ተጓድሏል በሚል በውሳኔው ቅር ተሰኝቶ ይግባኙን ለበላይ… Read More የጉዳት ካሳ ለዛፍ? (ፍርድ በግጥም)

ሚዛናዊ የግብረ ስጋ ግንኙነት (አስገራሚ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች #3)

ለመሆኑ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ከህግ አንፃር የተፈቀደው የግብረ ስጋ ግንኙነት አቅጣጫ (position) የትኛው ነው? በዶ እና ሞ (Doe Vs. Moe) መካከል በአሜሪካ ማሳቹሴትስ ግዛት የተካሄደ የይግባኝ ክርክር እና ውሳኔ ለዚህ ምላሽ የሚሰጥ ይመስላል፡፡ በመዝገቡ ላይ ይግባኝ ባይ የሆነው ግለሰብ “ፍቅረኛዬ የግብረስጋ ግንኙነት ስናደርግ ተገቢና ተስማሚ ያልሆነ አቅጣጫ እንድንጠቀም በማድረግ /በግልፅ አስገደደችኝ ባይልም ወትውታና ገፋፍታ… Read More ሚዛናዊ የግብረ ስጋ ግንኙነት (አስገራሚ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች #3)

በዓለም አጭሩ የፍርድ ቤት ውሳኔ!

በአሜሪካ በዴኒ እና ራዳር ኢንዱስትሪ መዝገብ (Denny Vs. Redar Industries)በሚቺጋን የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ በዓለማችን አጭሩ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተመዝግቧል፡፡ የውሳኔው ይዘት የአማርኛ ትርጉም እንዲህ ይነበባል፡፡ “ይግባኝ ባይ በዚህ ጉዳይ የተነሳውን የፍሬ ነገር ሁኔታ ከሬንፍሮ እና ሂጊንስ (Renfroe Vs. Higgins) ለመለየት ተሞክሯል፡፡ አልቻለም፡፡ እኛን አልቻልንም ጸንቷል፡፡ ኪሳራ ለመልስ ሰጭ፡፡” ሆኖም ይህ ሪከርድ በድሬዳዋ… Read More በዓለም አጭሩ የፍርድ ቤት ውሳኔ!

የጉዳት ካሳ ለዛፍ? (ፍርድ በግጥም #2)

በፊሸር እና ሎው (Fisher Vs. Lowe) መዝገብ ከሳሽ በአሜሪካ ሚቺጋን የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበ ክስ ተከሳሹ መኪናውን እየነዳ የከሳሽን የዋርካ ዛፍ ገጭቶ ጉዳት ስላደረሰ ካሳ እንዲከፈለው የሚጠይቅ  ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ታዲያ ክሱን ውድቅ ያደርግና ተከሳሽን በነፃ ያሰናብተዋል፡፡ በጣም በሚወደው ዛፍ ላይ ጉዳት  መድረሱ ያንገበገበው ከሳሽ ግን ፍትህ ተጓድሏል! በሚል በውሳኔው ቅር ተሰኝቶ ይግባኙን ለበላይ ፍርድ… Read More የጉዳት ካሳ ለዛፍ? (ፍርድ በግጥም #2)

ቲማቲም አትክልት ነው ወይስ ፍራፍሬ?

አንዳንዴ በተለመደው ዕለታዊ የኑሮ እንቅስቃሴ ቀላል ግምት የሚሰጣቸው አከራካሪ ጉዳዮች በፍርድ ቤት ጭብጥ ሆነው ሲቀርቡ መሰረታዊ በሆኑ የግል እና የንብረት መብቶች ላይ ትልቅ ልዩነት ያመጣሉ፡፡ አሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደረስ የደረሰ አንድ ጉዳይ ቲማቲም አትክልት ነው ወይስ ፍራፍሬ? የሚለው ጥያቄ የክርክሩ ዋነኛ መሠረታዊ ጭብጥ ሆኖ ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ እ.አ.አ በ1883 ዓ.ም. የወጣው የታሪፍ ህግ… Read More ቲማቲም አትክልት ነው ወይስ ፍራፍሬ?

ለማነው የተወሰነው?

የሰበር መ/ቁ 38506 ግንቦት 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ አመልካች፡- 1. አቶ አማኑኤል ነጋሪ 2. ወ/ሮ ማርታ ነጋሪ      ጠ/ጌታቸው ዲኪ 3. አቶ ዳንኤል ነጋሪ ተጠሪ፡- 1. የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ነ/ፈጅ ማህለት ዳዊት ቀረቡ 2. ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 መስተዳድር የቀረበ የለም 3. አቶ ዘላለም… Read More ለማነው የተወሰነው?

በእግዚአብሔርና በሰይጣን ላይ የቀረቡ ክሶች

የሰው ልጅ ከእንስሳት የሚለይበት ዐቢይ ነጥብ ከሳሽነቱ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም (ሊሆንም ይችላል) ሰው ከሳሽ ፍጡር ነው የክሱና የከሳሹ ብዛት ብቻ ሳይሆን የክሱ ዓይነትና ይዘት ሰዎች ከሙግት ጋር ስላላቸው ጥብቅ ቁርኝት አስረጂ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል በዓለማችን ላይ እጅግ በጣም በርካታ ፌዝ መሳይ ክሶች ቢኖሩም በእግዚአብሔርና በሰይጣን ላይ የቀረቡት ክሶች ግን በአውራነት ሊፈረጁ ይችላሉ ነገሩ የፌዝ… Read More በእግዚአብሔርና በሰይጣን ላይ የቀረቡ ክሶች