ልገሳና ልመና (የጠበቃ ቀልድ)

የኅብረተሰቡን የልማት ችግር በመቅረፍ ላይ የተሰማራ አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት የከተማው ነዋሪ ሁሉ የቻለውን ያህል ሲረዳ አንድ እጅግ የተሳካለት ሀብታም ጠበቃ ግን ምንም መዋጮ እንዳልሰጠ ሲረዳ የገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሊቀመንበሩን ለገንዘብ ጥያቄ ወደ ጠበቃው ይልካል፡፡ ሊቀመንበሩ ወደ ጠበቃው ቢሮ ሲገባ የትህትና ሰላምታ ካቀረበ በኋላ ቁጭ ብሎ የመጣበትን ጉዳይ ማስረዳት ጀመረ፡፡ “ምንም እንኳን የእርስዎ ዓመታዊ ገቢ… Read More ልገሳና ልመና (የጠበቃ ቀልድ)

ዘብ.ጥያ (የጠበቃ ቀልዶች)

ከአሰሪው ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አጭበርብሮ ወሰዷል ተብሎ በፖሊስ የተያዘ አንድ ሰው በውድ ዋጋ የቀጠረውን ጠበቃ ነፃ ለመውጣት ያለውን ዕድል ይጠይቀዋል፡፡ ጠበቃውም ሰውየውን በማረጋጋት “ግድ የለህም ይህን ሁሉ ገንዘብ ይዘህማ ዘብጥያ አትወርድም!” ይለዋል፡፡ ጠበቃው እውነት ብሏል፡፡ ሰውየው ጥፋተኛ ተብሎ ዘብጥያ ሲወርድ ስባሪ ሳንቲም እንኳን አልቀረውም ነበር::

የችሎት ቀልዶች

በአንድ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ ዐቃቤ ህጉ “ጌታዬ ይህ ድርጊት የተፈጸመው ተስተናጋጅ ጢም ብሎ በሞላበት ሬስቶራንት ውስጥ ነው፡፡” ብሎ መናገር ሲጀምር በነገሩ የተደመሙት ዳኛ “በእኔ ተሞክሮ ግን ይህን መሰል ድርጊቶች የሚፈጸሙት ተስተናጋጅ በሌለበትና ሬስቶራንቱ ዝግ በሚሆንበት ጊዜ ነው፡፡” ሲሉት ዐቃቤ ህጉ ነገረኛ ቢጤ ነበረና “አይ ጌታዬ! እኔ እንኳን እንደዛ ዐይነት ተሞክሮ የለኝም!” በማለት የተከበሩት ዳኛ… Read More የችሎት ቀልዶች

የጫት ቀለብ (የችሎት ገጠመኝ)

ሐረር ውስጥ በቀረበ አንድ የ’ልጅ ቀለብ ይቆረጥልኝ’ ክስ ፍርድ ቤቱ የተከሳሹን ወርሃዊ የደመወዝ ገቢ መሠረት በማድረግ ቀለብ እንዲቆረጥ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ሆኖም ተከሳሽ በፍርድ ቤቱ የተቆረጠበት የገንዘብ መጠን ፈጽሞ አልዋጥልህ ይለዋል፡፡ ስለሆነም የይግባኝ አቤቱታ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ያቀርባል፡፡ ተከሳሹ በይግባኝ አቤቱታው ላይ ቅሬታውን ሲያሰማ ‹‹ የተከበረው ፍርድ ቤት በዚህ የኑሮ ውድነት ደመወዝ ከምግብና ከበርጫ እንደማታልፍ… Read More የጫት ቀለብ (የችሎት ገጠመኝ)

የ(ተከላካይ) ጠበቃ ቀልዶች

ዳኛው ተከሳሹን “ፍርድ ቤቱ ተከላካይ ጠበቃ እንዲያቆምልህ ትፈልጋለህ?” ሲሉ ይጠይቁታል ተከሳሽ—“አይ በራሴ ብከራከር እመርጣለሁ፡፡ የቀረበበኝ ክስ እኮ በጣም ከባድ ነው!!!፡፡” * * ** *  *** ተከሳሽ– “የተከበረው ፍርድ ቤት ሌላ ተከላካይ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ!” ዳኛ –“ምንድነው ምክንያትህ” ተከሳሽ –“ይሄኛው ተከላካይ ጠበቃ የኔን ጉዳይ ችላ ብሎታል፡፡” ዳኛ– (ወደ ተከላካይ ጠበቃ ዞረው)  “እህ! ለተከሳሹ ቅሬታ የምትለው ነገር… Read More የ(ተከላካይ) ጠበቃ ቀልዶች

ይግባኝ! ይግባኝ! አሁንም ይግባኝ! (የችሎት ገጠመኝ)

ከሳሽ ሆነው የቀረቡት ሴት በዕድሜ ጠና ያሉ ናቸው፡፡ ታዲያ በችሎት አንዴ መናገር ከጀመሩ የሚያስቆማቸው የለም፡፡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ለእሳቸው እንዲሰጥ ችሎት በቀረቡ ቁጥር መወትወት ስራቸው ነው፡፡ ዳኛው ዕድሜያቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት በጀመሩ ቁጥር በቀስታ ለማረጋጋት ይሞክራሉ፡፡ በመጨረሻ መዝገቡ ለውሳኔ ተቀጥሮ ቀጠሮው ሲደርስ ውሳኔው ተነበበና የእኚህ ከሳሽ ክስ ውድቅ ተደረገ፡፡ ከሳሽ እስከ መጨረሻዋ… Read More ይግባኝ! ይግባኝ! አሁንም ይግባኝ! (የችሎት ገጠመኝ)

አተርፍ ባይ (የጠበቃ ቀልዶች #6)

የጠበቃ ውሻ የታሰረበትን ገመድ በጥሶ ከቤት በመውጣት በቀጥታ ወደ አቅውራቢያው ስጋ ቤት ካመራ በኋላ ሙዳ ስጋ በጭቆ ያመልጣል፡፡ በውሻው ድርጊት የበገነው የስጋ ቤቱ ባለቤት በቀጥታ ወደ ውሻው ባለቤት ጠበቃ ቢሮ ካመራ በኋላ የሚከተለውን ጥያቄ ይጠይቀዋል፡፡ “የታሰረበትን ገመድ የፈታ ውሻ ከኔ ስጋ ቤት ስጋ ሰርቆ ቢሄድ የውሻውን ባለቤት የስጋዬን ዋጋ ልጠይቀው እችላለሁ?” ጠበቃውም በእርጋታ ካዳመጠ በኋላ… Read More አተርፍ ባይ (የጠበቃ ቀልዶች #6)

የጠበቃ ቀልዶች #5

አንድ ጠበቃ በአንዲት ትንሽ የገጠር ከተማ የገጠሩን ውበት እደነቀ ይንሸራሸር ነበር፡፡ ትንሽ መንገድ ከሄደ በኋላ ከመንገዱ ጠርዝ ላይ አደጋ የደረሰ በሚመስል መልኩ ሰዎች ተሰብስበው ግርግር ሲፈጥሩ ይመለከታል፡፡ ወዲያውኑ በዛ ቦታ ላይ የመኪና አደጋ እንደደረሰ የጠበቃ ቀልቡ ከነገረው ነገር ተነስቶ ድምዳሜ ላይ ደረሰ፡፡ በአደጋው ቦታ ዙሪያ ወደተኮለኮሉት ሰዎች በመጠጋት የአደጋውን ዓይነትና ሁኔታ ለማጣራት ቢንጠራራም መግቢያ ቀዳዳ… Read More የጠበቃ ቀልዶች #5

ነይ ንኪኝ! (የችሎት ገጠመኝ)

በወንጀል ተከሳሽ የሆነው ግለሰብ በቀጠሮው ቀን ባለመቅረቡ ዋሱ በፍርድ ቤቱ ተጠርቶ ይመጣል፡፡ በስራ ብዛት ይሁን በሌላ ምክንያት በፊታቸው ላይ መሰላቸት ጎልቶ የሚታባቸው ዳኛ ፊት ለፊታቸው የቆመውን ዋስ ስሙን ይጠይቁታል፡፡ ዋስ ስሙን ተናገረ፡፡ መፍረድ ብቻ ሳይሆን ማረጋገጥም የዳኞች ስራና ግዴታ ነውና እኚህ ዳኛም ማንነትህን እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ? መታወቂያ አለህ? ሲሉ ዋሱን ያፋጡታል፡፡ ዋሱ መታወቂያውን ረስቶ ኖሮ… Read More ነይ ንኪኝ! (የችሎት ገጠመኝ)

የአንድ እሳት የላሰ ጠበቃ ታሪክ

የሚቀጥለውን ትረካ አንዳንድ ከሳሾችና ተከሳሾች ነገሩ እውነት ሲሉ ቢደመጥም እውነተኛነቱ በገለልተኛ ጠበቃ አልተረጋገጠም፡፡ አሜሪካ ውስጥ አንድ ጠበቃ በዓለም ገበያ ላይ ብዙም የማይገኝ ውድ ሲጋራ ከገዛ በኋላ ለንብረቱ በጣም በመሳሳት የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ ይገባለታል፡፡ የኢንሹራንስ ፖሊሲ በገዛ አንድ ወር በማይላ ጊዜ ውስጥ ጠበቃው የመጀመሪያ ዙር አረቦን /ፕሪሚየም/ እንኳን ሳይከፍል ኢንሹራንስ የተገባላቸውን 24ቱንም ሲጋራዎች ሁሉ በየቀኑ እያጨሰ… Read More የአንድ እሳት የላሰ ጠበቃ ታሪክ