የችሎት ቀልዶች

በአንድ ከፍተኛ ትኩረት በሳበ የሙስና ወንጀል ክስ ጉዳይ ጠበቃው ምስክሩን የመስቀለኛ ጥያቄ ውርጅብኝ ያወርድባቸዋል፡፡ ምስክሩ ትልቅ ሰው ስለሆኑ ጠበቃው በአንቱታ ጥያቄውን ይጠይቃል፡፡ “በዚህ ጉዳይ ላይ በጥቅም ተደልለው 5,000 ብር ጉቦ ተቀብለዋል፡፡ እውነት ነው?” ምስክሩ ግን ጥያቄውን ያልሰሙ በመምሰል ዝም ብለው ወደ ዳኛው አቅጣጭ  መስኮት መስኮቱን ማየት ጀመሩ፡፡ “5,000 ብር ጉቦ አልተቀበሉም ወይ!?ይመልሱ እንጂ!”  ምስክሩ አሁንም… Read More የችሎት ቀልዶች

የጠበቃ ቀልዶች (#4)

አንድ ጀማሪ ጠበቃ ባለጉዳይ ወደ ቢሮው እየመጣ መሆኑን በመስኮት ተመለከተና ገበያውን ለማዋደድ ቶሎ ብሎ ስልኩን አንስቶ መነጋገር ይጀምራል፡፡ “ይቅርታ ያድረጉልኝ ጌታዬ! መዝገብ በመዝገብ ተደራርቦብኝ በስራ ጫና ተወጥሬአለሁ፡፡ የእርስዎን ጉዳይ ለማየት ቢያንስ የአንድ ወር ጊዜ ያስፈልገኛል፡፡ “በመቀጠል ስልኩን ዘጋና ፊት ለፊቱ ተገትሮ የሚጠብቀውን ባለጉዳይ ቀና ብሎ “እሺ ምን ልርዳህ?” ሲል ይጠይቀዋል፡፡ ሰውየውም “ምንም፡፡ የተቆረጠውን ስልክዎትን ለመቀጠል… Read More የጠበቃ ቀልዶች (#4)

የሰው ሀቅ! (የጠበቃ ቀልዶች #3)

  አንድ ሰው በመኪና ስርቆት ተከሶ ከረጅምና እልህ አስጨራሽ የፍርድ ቤት ሙግት በኋላ በነፃ ይለቀቃል፡፡ ያንኑ ቀን ማታ ጉዳዩን ሲያስችሉ ወደነበሩት ዳኛ ዘንድ ያመራና “ጌታዬ! ጠበቃዬ እንዲታሰር ዋራንት እንዲቆረጥልኝ እፈልጋለሁ” ይላቸዋል፡፡ ዳኛውም ተገርመው “ነፃ እንድትወጣ አደገረህ፡፡ ለምንድነው እንዲታሰር የምትፈልገው?” ሲሉ ይጠይቁታል “ጌታዬ እሱ የሰራኝ ጉድ!” ብሎ ጀመረና “ለጥብቅና የምከፍለው ገንዘብ ስላልነበረኝ የሰረቅኳትን መኪና ያለርህራሄ ወሰደብኝ”… Read More የሰው ሀቅ! (የጠበቃ ቀልዶች #3)

ቻርጅ እና ቻርጀር

      በሞባይል ስልክ ስርቆት ተጠርጥሮ ክስ ቀረበበት አንድ  ግለሰብ በቀጠሮው ቀን ፍርድ ቤት ሲቀርብ ዳኛው ‹‹ቻርጁ ደርሶሃል?›› ሲሉ ይጠይቁታል፡፡ ምን ያለበት ምን አይችልም እንዲሉ የዳኛውን ጥያቄ በወጉ ያልተረዳው ተከሳሽ  ‹‹ የምን ቻርጀር!? እኔ የወሰድኩት ሞባይል ብቻ ነው›› በማለት ፈጣን ቃሉን ሰጥቷል፡፡ ዳኛው ተከሳሹን “ፍርድ ቤት ተከላካይ ጠበቃ እንዲያቆምልህ ትፈልጋለህ?” ሲሉ ይጠይቁታል ተከሳሽ—“አይ በራሴ… Read More ቻርጅ እና ቻርጀር

ሟችን መበቀል (የጠበቃ ቀልዶች #3)

አንድ ጠበቃ በጣም ካረጀ በኋላ ይሞታል፡፡ ጠበቃው ከሞተ በኋላ አንድ ሰው ማንነቱን ደብቆ ጠበቃውን ማናገር እንደሚፈልግ በመግለፅ በተደጋጋሚ ወደ ጠበቃው ቢሮ ስልክ ይደውላል፡፡ የፀሐፊዋ የዘወትር ምላሽ “ይቅርታ ጌታየዬ! ሞቷል!” የሚል ነበር፡፡ ሆኖም ደዋዩ መደወሉን አላቋረጠም፡፡ በመጨረሻም በነገሩ ግራ የተጋባችው ፀሐፊ የደዋዩ  ድምጽ አንድ መሆኑን ስትረዳ ማን እንደሆነና ለምን በተደጋጋሚ እንደሚደውል ትጠይቀዋለች፡፡ የደዋዩ ምላሽ—-“የሱ ረዳት ነበርኩኝ… Read More ሟችን መበቀል (የጠበቃ ቀልዶች #3)

የተከበረችዋ ፍርድ ቤቷ!

በየትም አገር ቢሆን ፍርድ ቤት ይከበራል፡፡ ይህ የፍርድ ቤት ክብር ጉዳይ ለብዙ ሰዎች ምቾት አይሰጣቸውም፡፡ በተለይ በኛ ሀገር አብዛኛው ሰው የፍርድ ቤት ክብርን የሚያይዘው ከፍርሀት ጋር ነው፡፡ ሆኖም ፍርድ ቤቱ በወጉና በስርዓቱ ዳኝነቱን እንዲያከናውን ሊከበር እንጂ ሊፈራ አይገባውም፡፡ ይኸው የፍርድ ቤት ክብር ተምሳሌታዊ በሆነ መልኩ ከሚገለጽበቸው መንገዶች አንዱ በክርክር ወቅት ፍርድ ቤት የሚጠራበት የአክብሮት ስያሜ… Read More የተከበረችዋ ፍርድ ቤቷ!

ሰጥቶ መቀበል! (የጠበቃ ቀልዶች#2)

ጠበቃ ሐኪምና የባንክ ሰራተኛ የድሮ ወዳጃቸውን ሊቀብሩ ከአስከሬኑ አጠገብ ቆመዋል፡፡ በሀዘናቸው መሐል የባንክ ሰራተኛው ‹‹በኛ ባህል መሠረት ለሟች ለሰማይ ቤት የሚሆነው ትንሽ ገንዘብ መስጠት ልማዳችን ነው፡፡ ስለዚህም ለምን የተቻለንን አንረዳውም?›› ሲል ሃሳብ ያቀርባል፡፡ በሃሳቡ ሁሉም በደስታ ተስማምተው መጀመሪያ የባንክ ሰራተኛው ከኪሱ ድፍን መቶ ብር አውጥቶ የሬሳ ሳጥኑ ውስጥ ሸጎጥ አደረገ፡፡ ሐኪሙም እንደዚሁ ድፍን መቶ ብር… Read More ሰጥቶ መቀበል! (የጠበቃ ቀልዶች#2)

የጠበቃ ቀልዶች #1

አንድ ጠበቃዎችን በመኪና በመግጨት ራሱን የሚያዝናና የከባድ መኪና ሹፌር ነበር፡፡ ሁሌ ጠበቃ በመንገድ ላይ ሲያይ መኪናውን ያጠመዘዝና ያለርህራሄ ከገጨው በኋላ ‘ድው!’ የሚል የግጭት ድምጽ ሲሰማ አንጀቱ ይደርሳል፡፡ አንድ ቀን መኪናውን እየነዳ ወደ ስራ ሲሄድ አንድ ቄስ መንገድ ዳር ቆመው ሲያይ ‘ዛሬ እንኳን ደግ ልስራ !’ ብሎ በማስብ መኪናውን ያቆምላቸዋል፡፡ ‹‹ወዴት ነው የሚሄዱት አባት?” ይጠይቃቸዋል፡፡ ‹‹ፊት… Read More የጠበቃ ቀልዶች #1

ችሎቱ ይወድሻል!

እውነተኛነቱ ያልተረጋገጠ አንድ የችሎት ገጠመኝ እንዲህ ይነበባል፡፡ ተከሳሽ ሆና የቀረበችው ሴት መልኳ የሚማርክ ሰውነቷ የሚያማልል ዓይነት ነበረች፡፡ በዛ ላይ የለበሰችው ጉርድ ቀሚስ ተደማምሮ የዳኛውን ቀልብ ሳትስብ አልቀረችም፡፡ በችሎት የሚከናወነው አጭር የቃል ክርክር እንዳበቃ ከሳሽና ተከሻስ ከችሎት /ጉዳዩ የሚታው በዳኛው ቢሮ ውስጥ ነበር/ ሊወጡ ሲያመሩ ዳኛው ተከሳሽ ወደኋላ እንድትቀር ምልክት ይሰጧታል፡፡ ድንጋጤ የተሰማት ተከሳሽ የዳኛውን ትዕዛዝ… Read More ችሎቱ ይወድሻል!

የዱር አራዊት…!

ችሎቱ የተሰየመባት ክፍል ጠባብ ስለነበረች ባለጉዳዮች ከውጭ ተኮልኩለው ተራቸውን ይጠባበቃሉ ተራ የደረሰው ከሳሽና ተከሳሽ ወይም ሌላ ባለጉዳይ በችሎት ጸሃፊዋ አማካይነት ጥሪ እየተደረገለት ይገባል ችሎት ጸሃፊዋ ሁሉም እንዲሰማው ጮክ እያለች ትጣራለች ተራቸውን ከሚጠባበቁት ተከራካሪዎች መካከል የዱር አራዊት ጥበቃና እንክብካቤ ድርጅት አንዱ ሲሆን ተራው ደረሰውና ችሎት ጸሃፊዋ ስሙን አሳጥራ ‘የዱር አራዊት!’ ብላ ከመጣራቷ ከመቅፅበት ከባለጉዳዮች መካከል አንድ… Read More የዱር አራዊት…!