ሚዛናዊ የግብረ ስጋ ግንኙነት (አስገራሚ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች #3)

ለመሆኑ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ከህግ አንፃር የተፈቀደው የግብረ ስጋ ግንኙነት አቅጣጫ (position) የትኛው ነው? በዶ እና ሞ (Doe Vs. Moe) መካከል በአሜሪካ ማሳቹሴትስ ግዛት የተካሄደ የይግባኝ ክርክር እና ውሳኔ ለዚህ ምላሽ የሚሰጥ ይመስላል፡፡ በመዝገቡ ላይ ይግባኝ ባይ የሆነው ግለሰብ “ፍቅረኛዬ የግብረስጋ ግንኙነት ስናደርግ ተገቢና ተስማሚ ያልሆነ አቅጣጫ እንድንጠቀም በማድረግ /በግልፅ አስገደደችኝ ባይልም ወትውታና ገፋፍታ… Read More ሚዛናዊ የግብረ ስጋ ግንኙነት (አስገራሚ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች #3)

ነይ ንኪኝ! (የችሎት ገጠመኝ)

በወንጀል ተከሳሽ የሆነው ግለሰብ በቀጠሮው ቀን ባለመቅረቡ ዋሱ በፍርድ ቤቱ ተጠርቶ ይመጣል፡፡ በስራ ብዛት ይሁን በሌላ ምክንያት በፊታቸው ላይ መሰላቸት ጎልቶ የሚታባቸው ዳኛ ፊት ለፊታቸው የቆመውን ዋስ ስሙን ይጠይቁታል፡፡ ዋስ ስሙን ተናገረ፡፡ መፍረድ ብቻ ሳይሆን ማረጋገጥም የዳኞች ስራና ግዴታ ነውና እኚህ ዳኛም ማንነትህን እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ? መታወቂያ አለህ? ሲሉ ዋሱን ያፋጡታል፡፡ ዋሱ መታወቂያውን ረስቶ ኖሮ… Read More ነይ ንኪኝ! (የችሎት ገጠመኝ)

ወርቃማ የላቲን አባባሎች #2

Nulli vendemus, nilli negabimus, aut differemus rectum vel justitiam. ፍትህን ለማንም አንሸጥም፣ ለማንም አንነፍግም፣ ለማንም አናዘገይም፡፡ Optimus interpretandi modusest sic legs interpretare ut leges legibus. በጣም ምርጥ የሆነው ህጎችን የመተርጎም ዘዴ ህጎችን እርስ በርሳቸው እንዲጣጣሙ ማድረግ ነው፡፡ Parum est latam esse sententiam, nisi mandetur executioni በተግባር ካልተፈጸመ ፍርድ መስጠቱ ብቻ በራሱ በቂ አይደለም፡፡ Plus valet… Read More ወርቃማ የላቲን አባባሎች #2

የአንድ እሳት የላሰ ጠበቃ ታሪክ

የሚቀጥለውን ትረካ አንዳንድ ከሳሾችና ተከሳሾች ነገሩ እውነት ሲሉ ቢደመጥም እውነተኛነቱ በገለልተኛ ጠበቃ አልተረጋገጠም፡፡ አሜሪካ ውስጥ አንድ ጠበቃ በዓለም ገበያ ላይ ብዙም የማይገኝ ውድ ሲጋራ ከገዛ በኋላ ለንብረቱ በጣም በመሳሳት የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ ይገባለታል፡፡ የኢንሹራንስ ፖሊሲ በገዛ አንድ ወር በማይላ ጊዜ ውስጥ ጠበቃው የመጀመሪያ ዙር አረቦን /ፕሪሚየም/ እንኳን ሳይከፍል ኢንሹራንስ የተገባላቸውን 24ቱንም ሲጋራዎች ሁሉ በየቀኑ እያጨሰ… Read More የአንድ እሳት የላሰ ጠበቃ ታሪክ

የችሎት ቀልዶች

በአንድ ከፍተኛ ትኩረት በሳበ የሙስና ወንጀል ክስ ጉዳይ ጠበቃው ምስክሩን የመስቀለኛ ጥያቄ ውርጅብኝ ያወርድባቸዋል፡፡ ምስክሩ ትልቅ ሰው ስለሆኑ ጠበቃው በአንቱታ ጥያቄውን ይጠይቃል፡፡ “በዚህ ጉዳይ ላይ በጥቅም ተደልለው 5,000 ብር ጉቦ ተቀብለዋል፡፡ እውነት ነው?” ምስክሩ ግን ጥያቄውን ያልሰሙ በመምሰል ዝም ብለው ወደ ዳኛው አቅጣጭ  መስኮት መስኮቱን ማየት ጀመሩ፡፡ “5,000 ብር ጉቦ አልተቀበሉም ወይ!?ይመልሱ እንጂ!”  ምስክሩ አሁንም… Read More የችሎት ቀልዶች

አንታራም የጠበቃ ጥያቄዎች #2

እውነተኛ የፍርድ ቤት ጥያቄና መልሶች ጥያቄ – ዶክተር!የሬሳ ምርመራውን ከማድረግህ በፊት የልብ ምት መኖር አለመኖሩን አረጋግጠሃል? መልስ – አላረጋገጥኩም፡፡ ጥያቄ – ትንፋሽ መኖሩን አለመኖሩን አረጋግጠሃል? መልስ – አላረጋገጥኩም፡፡ ጥያቄ – ስለዚህ የሬሳ ምርመራውን ስትጀምር በሽተኛው በህይወት ነበር ለማለት ይቻላላ? መልስ – አይቻልም፡፡ ጥያቄ – እንዴት እርግጠኛ መሆን ትችላለህ? ዶክተር? መልስ – ምክንያቱም አንጎሉ አጠገቤ ከነበረው… Read More አንታራም የጠበቃ ጥያቄዎች #2

በዓለም አጭሩ የፍርድ ቤት ውሳኔ!

በአሜሪካ በዴኒ እና ራዳር ኢንዱስትሪ መዝገብ (Denny Vs. Redar Industries)በሚቺጋን የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ በዓለማችን አጭሩ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተመዝግቧል፡፡ የውሳኔው ይዘት የአማርኛ ትርጉም እንዲህ ይነበባል፡፡ “ይግባኝ ባይ በዚህ ጉዳይ የተነሳውን የፍሬ ነገር ሁኔታ ከሬንፍሮ እና ሂጊንስ (Renfroe Vs. Higgins) ለመለየት ተሞክሯል፡፡ አልቻለም፡፡ እኛን አልቻልንም ጸንቷል፡፡ ኪሳራ ለመልስ ሰጭ፡፡” ሆኖም ይህ ሪከርድ በድሬዳዋ… Read More በዓለም አጭሩ የፍርድ ቤት ውሳኔ!

የጉዳት ካሳ ለዛፍ? (ፍርድ በግጥም #2)

በፊሸር እና ሎው (Fisher Vs. Lowe) መዝገብ ከሳሽ በአሜሪካ ሚቺጋን የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበ ክስ ተከሳሹ መኪናውን እየነዳ የከሳሽን የዋርካ ዛፍ ገጭቶ ጉዳት ስላደረሰ ካሳ እንዲከፈለው የሚጠይቅ  ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ታዲያ ክሱን ውድቅ ያደርግና ተከሳሽን በነፃ ያሰናብተዋል፡፡ በጣም በሚወደው ዛፍ ላይ ጉዳት  መድረሱ ያንገበገበው ከሳሽ ግን ፍትህ ተጓድሏል! በሚል በውሳኔው ቅር ተሰኝቶ ይግባኙን ለበላይ ፍርድ… Read More የጉዳት ካሳ ለዛፍ? (ፍርድ በግጥም #2)

የጠበቃ ቀልዶች (#4)

አንድ ጀማሪ ጠበቃ ባለጉዳይ ወደ ቢሮው እየመጣ መሆኑን በመስኮት ተመለከተና ገበያውን ለማዋደድ ቶሎ ብሎ ስልኩን አንስቶ መነጋገር ይጀምራል፡፡ “ይቅርታ ያድረጉልኝ ጌታዬ! መዝገብ በመዝገብ ተደራርቦብኝ በስራ ጫና ተወጥሬአለሁ፡፡ የእርስዎን ጉዳይ ለማየት ቢያንስ የአንድ ወር ጊዜ ያስፈልገኛል፡፡ “በመቀጠል ስልኩን ዘጋና ፊት ለፊቱ ተገትሮ የሚጠብቀውን ባለጉዳይ ቀና ብሎ “እሺ ምን ልርዳህ?” ሲል ይጠይቀዋል፡፡ ሰውየውም “ምንም፡፡ የተቆረጠውን ስልክዎትን ለመቀጠል… Read More የጠበቃ ቀልዶች (#4)

የሰው ሀቅ! (የጠበቃ ቀልዶች #3)

  አንድ ሰው በመኪና ስርቆት ተከሶ ከረጅምና እልህ አስጨራሽ የፍርድ ቤት ሙግት በኋላ በነፃ ይለቀቃል፡፡ ያንኑ ቀን ማታ ጉዳዩን ሲያስችሉ ወደነበሩት ዳኛ ዘንድ ያመራና “ጌታዬ! ጠበቃዬ እንዲታሰር ዋራንት እንዲቆረጥልኝ እፈልጋለሁ” ይላቸዋል፡፡ ዳኛውም ተገርመው “ነፃ እንድትወጣ አደገረህ፡፡ ለምንድነው እንዲታሰር የምትፈልገው?” ሲሉ ይጠይቁታል “ጌታዬ እሱ የሰራኝ ጉድ!” ብሎ ጀመረና “ለጥብቅና የምከፍለው ገንዘብ ስላልነበረኝ የሰረቅኳትን መኪና ያለርህራሄ ወሰደብኝ”… Read More የሰው ሀቅ! (የጠበቃ ቀልዶች #3)