የአሠሪና ሠራተኛ ህግ በዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች እና የውጭ ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ላይ ያለው ተፈጻሚነት

መግቢያ የአንቀጽ 3(3) ሀ ድንጋጌ ይዘት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ወይም ኢትዮጵያ በምትፈራረማቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች አዋጁ ተፈፃሚ እንዳይሆን ሊወሰን እንደሚችል ይናገራል። ድንጋጌው በራሱ በግልጽ ወይም በተዘዋዋሪ የሚያገለው ሠራተኛ የለም። እስካሁን ድረስ ምክር ቤቱ በተሰጠው ስልጣን ተጠቅሞ ያወጣው ማግለያ ደንብ ካለመኖሩም በላይ የህጉ ተፈጻሚነት ወሰን በዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች አልተገደበም። የአሠሪና ሠራተኛ አዋጁ በዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችና የውጭ ዲፕሎማቲክ… Read More የአሠሪና ሠራተኛ ህግ በዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች እና የውጭ ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ላይ ያለው ተፈጻሚነት

የአሠሪና ሠራተኛ ህግ እና የውል ህግ ተዛምዶ

የአሠሪና ሠራተኛ ህግ እና የውል ህግ የአሠሪና ሠራተኛ ህግ የሥራ ውል እንደመሆኑ ለውል ህግ መሰረታዊ ደንቦች ይገዛል። ስምምነቱ በህግ ማዕቀፍ የሥራ ውል ተብሎ በሚጠራው የውል ዓይነት አማካይነት መልክ ይዞ ይቀረጻል። የሥራ ውል እንደማንኛውም ዓይነት ውል ሁሉ ለውል ህግ መሰረታዊ መርሆዎችና ደንቦች ተገዢ ነው። በፍ/ህ/ቁ 1676(1) ግልጽ ሆኖ እንደተደነገገው ውሎች ዓይነታቸው ሆነ ምክንያታቸው ማንኛውም ቢሆን በውል ህግ ጠቅላላ… Read More የአሠሪና ሠራተኛ ህግ እና የውል ህግ ተዛምዶ

ህጋዊ እና ህገ-ወጥ የሥራ ውል መታገድ ውጤት

የህጋዊ ዕገዳ ውጤት የዕገዳ ጊዜ ማብቃት የዕገዳ ምክንያት አለማብቃት የህገ-ወጥ ዕገዳ ውጤት የማስታወቅ ግዴታን መጣስ የባለስልጣኑን ውሳኔ መጣስ የሥራ ውል መታገድ የህጋዊ ዕገዳ ውጤት በህጉ ላይ በተዘረዘሩት አጥጋቢ ምክንያቶች የተነሳ ከሥራ ውል የሚመነጩ መብትና ግዴታዎች ለጊዜው መታገድ የሠራተኛውን የመስራት ግዴታ እና የአሠሪውን ደመወዝ የመክፈል ግዴታ ለጊዜው ቀሪ ያደርጋል። ከላይ ለመጠቆም እንደተሞከረው ዕገዳ የሥራ ውሉን ለጊዜው… Read More ህጋዊ እና ህገ-ወጥ የሥራ ውል መታገድ ውጤት

አሠሪና ሠራተኛ ህግ እና የፍትሐ ብሔር ስነ-ስርዓት ህግ

የስነ-ስርዓት ህግ ግብ በፍርድ ቤት የሚካሄዱ ክርክሮች ቀልጣፋ፤ ወጪ ቆጣቢና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንዲቋጩ ማስቻል ነው።  የዚህ ግብ መሳካት በተለይ በሥራ ክርክሮች ላይ የተለየ እንደምታ አለው። የሥራ ውል መቋረጥ በሠራተኛው እና በቤተሰቡ ዕለታዊ ኑሮ ላይ ከሚያሳድረው ከባድ ጫና አንጻር አሠሪው ላይ የሚያቀርባቸው የመብት ጥያቄዎች ሳይውሉ ሳያድሩ በፍጥነት መቋጨት ይኖርባቸዋል። ይህን እውን ለማድረግ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጁ… Read More አሠሪና ሠራተኛ ህግ እና የፍትሐ ብሔር ስነ-ስርዓት ህግ

የቅጥር ግንኙነት

ልውውጥ እና የመደራደር አቅም ግላዊ የሆነው የቅጥር ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ባህርያት ናቸው። በልውውጥ ግንኙነት (Exchange Relationship) ሠራተኛው ለሚያበረክተው አገልግሎት ክፍያ ይሰጠዋል። አሠሪው ደግሞ ለሚከፈለው ክፍያ አገልግሎት ያገኛል።… Read More የቅጥር ግንኙነት

የስራ መሪ – የፍርድ ቤት ስልጣን (የሰበር ውሳኔዎች ዳሰሳ ክፍል ሁለት)

የስራ መሪ – የፍርድ ቤት ስልጣን ላይ ላዩን ሲታይ የስራ መሪ የሚያቀርበውን ክስ ለማየት የዳኝነት ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት መለየት ቀላል ቢመስልም የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 377/96 የፍርድ ቤቶችን ስልጣን በተመለከተ እልባት ሳይሰጥ በቸልታ ካለፈው መሰረታዊ ጥያቄ አንጻር ሲታይ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ከመስጠታቸው በፊት ምክንያትን መሰረት ያደረገ ጥልቅ ፍተሻ ማድረግ እንዳለባቸው ይጠቁመናል፡፡ ከአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ… Read More የስራ መሪ – የፍርድ ቤት ስልጣን (የሰበር ውሳኔዎች ዳሰሳ ክፍል ሁለት)

የስራ መሪ -የሰበር ውሳኔዎች ዳሰሳ

የስራ መሪ የሰበር ውሳኔዎች ዳሰሳ ክፍል አንድ የስራ መሪ ትርጉም ለስራ መሪ የተሰጠው ትርጓሜ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 377/1996 አንቀጽ 2(ሐ) ላይ የተመለከተ ሲሆን በሰበር በተሰጡ ውሳኔዎች የድንጋጌውን ይዘት እንደወረደ ከመድገም ባለፈ ድንጋጌውን ለመረዳት የሚያስችል ተጨማሪ ማብራሪያ ወይም ትንተና አልተሰጠም ለምሳሌ በሰ.መ.ቁ. 42901 (አመልካች የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት እና ተጠሪ ወ/ሮ ንግሥት ለጥይበሉ ሐምሌ… Read More የስራ መሪ -የሰበር ውሳኔዎች ዳሰሳ

ሰራተኛው ለአሰሪው ያለበት ተጠያቂነት የህግ መሰረቱ

የሰበር መ/ቁ. 39471 ሐምሌ 29 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. ዳኞች ፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልዱ ሂሩት መለሠ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች ፡- ኤርሚያስ ሙሉጌታ – አልቀረቡም ተጠሪ ፡- በከልቻ ትራንስፖርት አ/ማ – ይልማ ገመቹ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡ ፍ      ር     ድ በዚህ መዝገብ የቀረበው የሰበር አቤቱታ አመልካች በተጠሪ ተቀጥሮ በሾፌርነት ሲሠራ በነበረበት ጊዜ… Read More ሰራተኛው ለአሰሪው ያለበት ተጠያቂነት የህግ መሰረቱ

ሰራተኞች ስላላቸው የቅድሚያ ክፍያ መብት

የሰ/መ/ቁ. 40921 የካቲት 26 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ አመልካች፡- አቢሲኒያ ባንክ (አ.ማ) ነ/ፈጅ ዱላ መራራ ተጠሪ፡– እነ አብዱ አህመድ (266 ሰዎች) ጠበቃ ምትኩ በዚህ መዝገብ የቀረበው አቤቱታ በመ/ቁጥር 42132 ከቀረበው አቤቱታ ጋር በስረ ነገርም ሆነ በጭብጥ ረገድ ተመሳሳይ በመሆኑ ሁለቱም መዛግብት ጐን ለጐን ተመርምረው ቀጥሎ… Read More ሰራተኞች ስላላቸው የቅድሚያ ክፍያ መብት

የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍ/ቤት ስልጣን

የፍ/ይ/መ/ቁጥር 57621 ሐምሌ 30 ቀን 2002ዓ.ም ዳኞች፡-  አስግድ ጋሻው ደስታ ገብሩ በላቸው አንሺሶ አመልካቾች፡- 1ኛ አቶ እምሩ አበጋዝ 2ኛ አቶ አለማየሁ ባይሴ 3ኛ ባሻ መሐመድ 4ኛ ጌታቸው ቶላ ተጠሪ፡- የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡ ው ሳ ኔ አመልካቾች ቀደም ሲል ለፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ የአስተዳደር ፍ/ቤት ያቀረቡት አቤቱታ የመድሀኒት ፈንድ አቅርቦት ኤጀንሲ በተባለ የፌዴራል… Read More የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍ/ቤት ስልጣን