ህግ እንዳበጁሽ


ሮበርት ኮህን የተባለ አንድ አሜሪካዊ ጠበቃ “ማወቅ የምፈልገው ህጉ ምን እንደሆነ ሳይሆን ዳኛው ማን እንደሆነ ነው” ሲል ተናግሮ ነበር፡፡
ዳኛ ማለት የወጣለት ደፋኝ ነው፡፡ ሕግ ቀዳዳ ሲኖራት ፣ ክፍተት ُከታየባት በሕግ ተርጓሚነት ሚናው ቀዳዳውን ይደፍናል ፡፡ ክፍተቱን ይሞላል፡፡ ሕግን የመተርጎም
ስራ ህግን የማበጀት ስራ ነው፡፡ ዳኛው ሕግን የማበጀት ተግባር የሚያከናውነው በዘፈቀደ ወይም እንዳሰኘው ሳይሆን በፍትህ ችቦ እየተመራ መሆን ይኖርበታል፡፡

ሄነሪ ሉዊስ ሜንከንነ የተባለ ፀሃፊ እንዳለው ዳኛ ማለት “የራሱን የፈተና ወረቀት የሚያርም የህግ ተማሪ” ማለት ነው፡፡ ዳኛው እርማቱን ሲከናውን ሁልጊዜ ለራሱ 10 ከ 10 የሚደፈን ከሆነ ውጤቱ ጉብዝናውን አያሳይም፡፡ ብቀቱ ያለው የእርማቱ ወይም የማበጀቱ ፍትሃዊነት በገሃድ ተገልጦ ሲታይ ብቻ ነው፡፡
ክፍተት ያለበት ህግ ሕግ በተለያዩ ዳኞች በተለያየ መንገድ ሊተረጎም ይችላል፡፡
ሆኖም ልዩነቱ የሃራምባና ቆቦ ያህል ሲራራቅ አልገናኝ አልቀራረብ ሲል ያኔ ወጥነት ይጠፋል፡፡ ዛሬ የተፈቀደ የነበረው ነገ የተከለከለ ይሆናል፡፡ ህጉ የሚለው ሳይሆን ዳኛው የሚለው ህግ ይሆናል፡፡ ህግ ሁን ያሉትን ይሆናል፡፡
ስለዚህ ህግ ምንድነው? ” ህግ በአሸዋ የተሰራ ገመድ ነው፡፡ ሲጠመዝዙት ይጠፋል”

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s