አስገራሚ ክሶች


አሜሪካ ውስጥ ማንም ሰው በማንም ሰው ላይ በማንኛውም ጉዳይ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ክስ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ የፌዝ የሚመስሉ ክሶች ፍርድ ቤት ፋይል ተከፍቶላቸው የሚቀርቡት በስራ ፈቶች ብቻ ሳይሆን ያወቁና የነቁ በሚባሉ ሰዎች ጭምር ነው፡፡ የፌዝ ክሶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመብዛታቸው የተነሳ ይህንኑ ለመከላከል (Citizens against lawsuit abuse) የሚባል ድርጅት ተቋቁሟል፡፡

ከነዚ የፌዝ የሚመስሉ ክሶች በምሳሌነት የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፡፡

በአሜሪካ ከቅዱስ ቶማስ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ውጤት ባለማምጣቱ ምክንያት የተባረረ አንድ ተማሪ በህግ ትምህርት ቤቱ ላይ ክስ አቅርቧል፡፡ የክሱ ምክንያት አለአግባብ ተባረርኩ በሚል ሳይሆን መጀመሪያውኑ ትምህርት ቤቱ እኔን መቀበል አልነበረበትም የሚል ነው፡፡ እንደ ከሳሹ ጠበቃ አገላለጽ የህግ ትምህርት ቤቱ የህግ ትምህርት ተምረው ለማጠናቀቅ በአማካይ ምንም ዕድል የማይኖራቸውን ተማሪዎች መጀመሪያውኑ መቀበል አልነበረበትም፡፡

 

የአንድ የህግ ታራሚ በክሱ ላይ መንግስት 5 ሚሊዬን ዶላር ካሳ እንዲከፍለው ጠይቋል፡፡ ከሳሽ ጉዳት ደረሰብኝ የሚለው በመንግስት ሳይሆን በራሱ ነው፡፡ ከሳሽ በክሱ እንደገለጸው ለራሱ መታሰር ምክንያት በመሆን የራሱን ሰብዓዊ መብት በመጣስ በራሱ ላይ ከፍ ያለ ጉዳትና ኪሳራ አድርሷል፡፡ ክሱን በመንግስት ላይ ያቀረበበት ምክንያትም ከሳሽ የህግ ታራሚ በመሆኑና በእስር ቤት ምንም ገቢ ስለሌለው ራሱ በራሱ ላይ ላደረሰው ጉዳት ራሱ ካሳ መክፈል ስለማይችል መንግስት በሱ ቦታ ሆኖ እንዲከፍልለት ነው፡፡ “ሰርቼ መክፈል ስለማልችል መንግስት እንደ እኔ ሆኖ እንዲከፍልልኝ እጠይቃለሁ፡፡” በማለት ነበር የደረሰበትን በደል በመግለጽ የካሳ ጥያቄውን ያቀረበው፡፡

 

አባትና እናት የአሜሪካ የነፃነት ቀን በዓልን አብረዋቸው እንዲያከብር የሚወዱት ልጃቸውን ይጋብዙታል፡፡ ልጅ ግብዣውን በደስታ ተቀብሎ በዓሉን በድምቀት ለማክበር በማሰብ ርችት ገዝቶ ይሄዳል፡፡ ከሰዓታት በኋላ በተደጋጋሚ የጠጣው መጠጥ አናቱ ላይ ወጥቶ ብትን ብሎ ይሰክራል፡፡ በስካር ውስጥ እንዳለ ይዞት የመጣውን ርችት ትዝ ይለውና ይለኩሰዋል፡፡ ሆኖም ርችቱ አልተኮስ ስላለው በስካር መንፈስ ሲነካካው ድንገት ተቀጣጥሎ ይፈነዳና መጠነኛ ጉዳት ያደርስበታል፡፡ ይህ ሰው ታዲያ የዋዛ አልነበረም፡፡ ስካሩ ሲለቀው ለደረሰበት ጉዳት ካሳ እንዲከፈለው በራሱ ወላጆች ርችቱን በሸጠለት ሰራተኛ እና ድርጅት ላይ ክስ አቅርቧል፡፡

 

አንድ ሌባ በሰው ንብረት ለመበልጸግ አጥር ደፍሮ ቤት ሰርስሮ አንድ ቤት ውስጥ ዘው ይላል፡፡ ሃሳቡ መኪና ለመስረቅ ነበርና በቀጥታ ያመራው ወደ መኪና ማቆሚያው ክፍል ነበር፡፡ ገና እንደገባ ለመግባት ቀላል የሆነለት በር ድንገት ይዘጋና ከፍቶ ለመውጣት ቢታገል ቢታገል ለመክፈት ፈጽሞ እምቢ ይለዋል፡፡ በአጋጣሚ ሆኖ የቤቱ ባለቤቶች ትንሽ ዘና ለማለት ወደ ሌላ ቦታ ሄደው ነበር፡፡ ሌባው ለአምስት ቀናት ያህል የሚላስ የሚቀመስ በሌለበት ክፍል ውስጥ “የእጁን እያገኘ!” ከረመ፡፡ በመጨረሻም በፖሊስ ተይዞ በስርቆት ወንጀል ክስ ሲቀርብበት እሱም በተራው ለአምስት ቀናት ያህል በመብልነና በውሃ እጦት ለደረሰበት ጉዳትና እንግልት የቤቱ ባለቤቶች ካሳ ሊከፍሉኝ ይገባል ሲል ዓይኑን በጨው ታጥቦ በፍርድ ቤት ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s