ለውይይት የቀረበው አዲስ የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ተቃውሞ ገጠመው


ለውይይት የቀረበው አዲስ የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ተቃውሞ ገጠመው     ሪፖርተር

የሕግ መምህራን ፈቃድ ማውጣት ይችላሉ
–    ፈቃድ ሳይኖረውና ፈቃዱን ሳያድስ ጥብቅና የቆመ በብርና በእስራት ይቀጣል
–    ጠበቆች ተከታታይ የሕግ ትምህርት እንዲወስዱ ይገደዳሉ
ለውይይት የቀረበው አዲሱ የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ በተሳታፊዎች ተቃውሞ ገጠመው፡፡

የረቂቁ የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ‹‹አጭር ርዕስ›› በሚለው ሥር ‹‹ይህ አዋጅ የጥብቅና ፈቃድና አስተዳደር አዋጅ›› ተብሎ ሊጠቀስ እንደሚችል ከሚገልጸው ጀምሮ፣ በቀረቡት የተለያዩ ክፍሎችና አንቀጾች ላይ የሚገኙት የአማርኛና የእንግሊዝኛ ፍቺዎች ፈጽሞ የማይገናኙና ትርጉማቸው የተለያዩ መሆናቸውን ተሳታፊዎቹ በተቃውሞ ገልጸዋል፡፡

ረቂቁ በ1992 ዓ.ም. ከወጣው የጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥ አዋጅ ያልተሻለና የወረደ በመሆኑ ለምን መሻሻል እንዳስፈለገ ጥያቄ ያቀረቡት ተሳታፊዎቹ፣ ረቂቁ የቋንቋ ችግር እንዳለበት በተደጋጋሚ ገልጸዋል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሦስት ቦታ ተከፍሎ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. በረቂቅ አዋጁ ላይ በተደረገ ውይይት፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራኖች፣ ከሁሉም ክፍሎች የተጋበዙ ባለድርሻ አካላት፣ የፍትሕ አካላት፣ የተለያዩ ፍርድ ቤቶች ዳኞች፣ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ተወካዮችና ጠበቆች በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

ረቂቁ ቀደም ብሎ የደረሳቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት መምህራን ባቀረቡት አስተያየት፣ በረቂቁ ‹‹በጥብቅና ሙያና ሥራ ላይ ለበርካታ ዘመናት የቆዩና ሰፊ ልምድ ያካበቱ፣ ምናልባትም ጠበቃ ከመሆናቸው በፊት በከፍተኛ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ የነበሩ ሰዎች ጭምር ለጥብቅና ፈቃድ የሚያመለክት እንደ አዲስ ፈተና ተፈትኖ ፈቃድ ያውጣ፤›› የሚለውን ‹‹ወደኋላ መመለስ ይሆናል›› በማለት ተቃውመዋል፡፡

ሙሉውን ዜና ሪፖርተር ላይ ያንብቡ

1 Comment

  1. yerosen berhanu says:

    Am happy to see this page

Leave a Comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s